በኮምቦልቻ ከተማ ቂርአት የሚቀሩ ደረሶችን አህባሾች ዋሃቢያ ናችሁ በማለት እንዲባረሩ እያደረጉ መሆናቸው ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ የካቲት 10/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ ኢልም በመቅራት ላይ የነበሩ ደረሶችን ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ከቂርአን ቦታ እንዲባረሩ እያደረጉ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
ባሳለፍነው ማክሰኞ የካቲት 7 2009 በኮምቦልቻ ከተማ ቀንደኛ የአህባሽ አቀንቃኝ የሆኑት አቶ ሙህዲን እና አቶ ኢብራሂም የሚባሉት ግለሰቦች ቂርአን በመቅራት ላይ የነበሩ በርካታ ደረሶችን ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ከቂርአን ቦታ እንዲባረሩ ማስደረጋቸው ታውቋል፡፡
በኮንቦልቻ ከተማ ሸይኽ መሐመድ ያሲን በሚባሉ አሊም ላይ ነህው ሲቀሩ የነበሩ ቁጥራቸው 27 የሚደርሱ ደረሶችን ዋሃብያ ናችሁ በሚል ከቂርአን ቦታው እንዲባረሩ ማስደረጋቸው ተዘግቧል፡፡
ሱንይ በመሆናቸው በብቻ ከቂርአን ቦታ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል እንዲፈናቀሉ የተደረጉት ጣሊበል ኢልሞች ከቂርአት ቦታው ከመባረር በተጨማሪ አራት የሚሆኑትን በሃሰት በመወንጀል በፖሊስ እንዲያዙ አስደርገው እንደነበር የአካባቢው ምንጮች ለፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
በፖሊስ እንዲታሰሩ ተደርገው የነበሩት አራት ሙስሊሞችም ወደ ፖሊስ ጣብያ ከተወሰዱ ቡሃላ በሰላም የተለቀቁ ሲሆን በኮምቦልቻ ከተማ አህለል ሱናዎች ቂርአት በሚቀሩበት ቦታ ሁሉ አህባሾች እንቅፋት እየሆኑባቸው መሆኑ ተገልፆል፡፡
ከተባረሩት ደረሶች መካከል አንዱን ደረሳ የኦነግ አባል ነው በሚል በሀሰት በመወንጀል ለማሳሰር ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ የቀረ ሲሆን በየቂርአት ቦታዎች ላይ የአህባሽን የተበላሸ እምነት ያልተቀበለው ሁሉ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ከቂርአት ቦታዎች እያባረሩ መሆናቸው ተዘግቧል፡፤
አቶ ኢብራሂም ወይንም አብረሃም በመባል የሚታወቀው ሰው የቦርቸሌ ኢማም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በኮምቦልቻ ከተማ ፅንፈኛ አህባሽ ከሆኑት መካከል አንዱ መሆኑ ተገልፆል፡፡
የአህባሽን የተበላሸ አቂዳ የማይከተለውን ሙስሊም ዋሃቢያ በሚል የሚፈርጁ ሲሆን የአህባሽ አቂዳ እስካልተቀበላችሁ ድረስ ካፊር በመሆናችሁ ከነሳራ እና ከአይሁድ ለይተን አናያችሁም እንደሚሏቸው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ በሚገኘው በሸይኽ መሐመድ ያሲን በሚሰጠው የነህዉ ትምህርት ላይ እንዳይቀሩ የተባረሩት እነዚህ ደረሶች በስነ ምግባራቸው እና በኢልማቸውየሚታወቁ ሲሆኑ ከቂርአት ቦታቸው ወደ ቤት ሲመለሱ በቃላቸው ሃዲስ እየሃፈዙ የሚጓዙ እንደነበር ታውቋል፡፡
አህባሾች በኮምቦልቻ ከተማ መስጂዶችን በመንግስት ድጋፍ በጉልበት ከሙስሊሙ ከነጠቁ ወዲህ የተበከለ አስተምህሮታቸውን በህዝቡ ላይ እየረጩ የሚገኝ ሲሆን የነሱን ብልሹ አቂዳ የማይከተለውን ሁሉ ካፊር በማለት ከመስጂድ እና ከቂርአት ቦታዎች እያፈናቀሉ መሆናቸው ተዘግቧል፡፤
በተያያዘ ዜና በዚሁ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው በአህባሾች የሚመራው የታላቁ ኡመር መስጂድ ቅጥር ግቢ ለአሮጌ ባጃጅ እና መኪኖች መጠገኛ እና ማሰባሰቢያነት መሰጠቱን የአካባቢው ሙስሊሞች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
በቦርከና ዳር በምዕራብ በኩል የሚገኘው ይህ መስጂድ ለረጅም አመታት ህዝበ ሙስሊሙን ሲያገለግል የቆየ ሲሆን መስጂዱም በህዝበ ሙስሊሙ መዋጮ መገንባቱ ይታወቃል፡፡
አህባሽ መራሹ መጅሊስ በኮምቦልቻ የሚገኙ መስጂዶችን በጉልበት ከተረከበ ወዲህ መስጂዶች ተገቢውን የሆነ ክብር እየተነፈጉ ሲሆን ለረጅም አመታት ህዝበ ሙስሊሙን ሲያገለግል የነበረው የኡመር መስጂድ ቅጥር ግቢም ለአሮጌ ባጃጆች መጠገኛ መሰጠቱ ተሰምቷል፡፤
ስለመስጂዱ የሚከራከር አካል ባለመኖሩ በመስጂዱ ቅጥር ግቢ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኘውን ቦታ ለአሮጌዳ ባጃጆች መጠገኛነት ሲሰጥ በምዕራብ በኩል ያለውን ቦታ ለተበላሹ መኪናዎች ማቆሚያ እና ለእስፖርት ማዘውተሪያነት መሰጠቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
የህዝበ ሙስሊሙን መስጂድ በማን አለብኝነት የአሮጌ ባጃጅ መጠገኛ እና ማጠራቀሚያ እንዲሆን ያደረገው አካል አህባሽ መራሹ መጅሊስ ይሁን የመንግስት አካል እስካሁን ግልፅ አለመሆኑ ታውቋል፡፤
አህባሽ መራሹ መጅሊስ ለኪሳቸው ማደለቢያነት በሚል መስጂዱን ሸንሽነው አከራይተውት ይሁን መንግስት ለልማት በሚል ወስዶት ይሁን የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩ የታወቀ ሲሆን ለረጅም አመታት ህዝበ ሙስሊሙን ሲያገለግል የቆየው የኡመር መስጂድ በተዳከመ ሁኔታ ላይ መገኘቱ የአካባቢው ሙስሊሞችን ማሳዘኑ ተዘግቧል፡፤

ተጨማሪ ምስል