በከድር መሐመድ  የክስ መዝገብ የተከሰሱት 19 ሙስሊም ወንድሞቻችን የ 5 አመት ከ 6 ወራት የእስራት ቅጣት ተበየነባቸው
 

በፍትህ ራዲዬ/ታህሳስ 25/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩


ከድር መሃመድ የክስ መዝገብ  ተከሰው ከአዲስ አበባ እና ከጅማ ከተማ በደህንነት ሃይሎች ታፍነው ለእስር የተዳረጉት 19 ሙስሊም ወንድሞቻችን የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔያቸውን ለመስማት በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት በዛሬው እለት  የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል  ቀርበው እንደነበር     የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

አቃቤ ህጉ ባቀረበባቸው ክስ መሰረት ፍርድ ቤቱ በሁሉም ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፈ ቡሃላ እንዲከላከሉ ብይን ቢያስተላልፍ ተከሳሾቹ በፍርድ ቤቱ ገለልተኝነት አመኔታ የሌላቸው በመሆኑ፣በቂሊንጦ ማረሚያ ቤትም እየተፈፀመባቸው ባለው ግፍ እና ስቃይ በማረሚያ ቤቱ ተጨማሪ ጊዜያትን   ለመቆየት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው  መከላከያ ምስክሮቻቸውን ማቅረባቸው ጥቅም የሌለው መሆኑን በማስረዳት መከላከያ እንደማያቀርቡ እና  ፍርድ ቤቱም የመጨረሻ የሚለውን የቅጣት ውሳኔ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ይታወቃል፡

ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪን እና ጋዜጠና ካሊድ መሐመድን ያካተት ይህ የክስ መዝገብ ኮሚቴውን በሃይል ለማስፈታት በማሴር፣ በአዲስ አበባ ፣በወልቂጤ እና በጅማ ከተሞች ህገ ወጥ ሰልፍ እና ብጥብት ለመቀስቀስ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ ነበር በሚል ጥፋተኛ ናቸው ሲል ፍርድ ቤቱ መበየኑ ይታወቃል፡፡

በሃሰት የተወነጀሉት ወንድሞቻችን በፀር ሽብር ህጉ አንቀፅ 7/1 እና በኢፌደሪ የወንጀል መቅጫ ህግ አንቀፅ 32/1 ሀ እና አንቀፅ 38/1 በመተላለፍ በሚል  ነው የጥፋተኝነት ብይን የተላለፈባቸው፡ :

በዚህ መሰረት በታህሳስ 12 በነበረው ችሎት በሁሉም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያሰተላለፈው ይኸው ፍርድ ቤት ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያቸውን እና የአቃቤ ህጉን የቅጣት ማቅለያ በቢሮ በኩል ለፍርድ ቤቱ ገቢ እንዲያደርጉ ማዘዙ ይታወሳል፡፡

 ፍርድ ቤቱ የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃቸውን ከተመለከተ ቡኋላ በደህንነቶች በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት  በዛሬው እለት  ታህሳስ 25 በሁሉም ተከሳሾች ላይ የ 5 አመት ከ 6 ወራ የእስራት ቅጣት እንደበየነባቸው ታውቋል፡፡

ለ 2አመታት በግፍ እስር ያሳፈለፉት እነዚህ ወንድሞቻችን ቀጣይ የእስር ጊዜያቸውን ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት በመሄድ  ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል

ሃስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል 

ተጨማሪ ምስል