በከሚሴ በኹለፋኡል ራሺዱን መስጂድ የሚገኘው መድረሰተ ሰላም 2ኛ ዙር የቁርአን ሃፊዞቹን አስመረቀ
ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 29/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በኦሮሚ ልዩ ዞን በከሚሴ ከተማ የሚገኘው መድረሰተ ሰላም ለ2ኛ ዙር የቁርአን ሃፊዞቹን ማስመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
የምረቃ ስነ ስርአቱ በከሚሴ ከተማ በሚገኘው በገልማ አባገዳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በርካታ የከተማው ህዝበ ሙስሊም በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ መካፈሉ ተዘግቧል፡፡
በከሚሴ ከተማ እና በዙሪያዋ የሚገኙ በርካታ ኡለሞች እና ኡስታዞችበምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ መካፈላቸው የተዘገበ ሲሆን መድረሳው ላለፉት ሁለት አመታት ሲያስተምራቸው የቆየውን የቁርአን ሂፍዝ ተማሪዎቹን በመደቀ ሁኔታ ማስረመቁ ታውቋል፡፡
ተመራቂ ተማሪዎቹ ነጭ ጀለብያ ፣ቀይ አማይማ እና ሰማያዊ ሪቫን በማድረግ በምረቃው ላይ የቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ፊት ሆነው ለምረቃቱ ድምቀት ሰጥተው እንደነበር ተዘግቧል፡፡
በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተለያዩ የዳዕዋ እና አዝናኝ ፕሮግራሞች የቀረቡ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪዎችም የሽልማት ፕሮግራም መካሄዱ ተገልፆል፡፡
በተመሳሳይ ዜናም በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው የመርከዝ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል የቁርዓን ሂፍዝ ማዕከል አራተኛ ዙር ተማሪዎቹን ማስመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
የምረቃ ስነ ስርአቱ በድሬዳዋ ከተማ በኡጋዝ ሐሰን አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን ጨምሮ ኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ እና ሌሎችም በክብር እንግድነት መካፈላቸው ተዘግቧል፡፡
ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እና ኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ ድሬዳዋ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይም የዳዕዋ ፕሮግራምማቅረባቸው ታውቋል፡፡
ከቁርአን ሃፊዞቹ ምረቃ በተጨማሪ በእለቱ ለመርከዙ ማጠናከሪያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም መካሄዱንም የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ተጨማሪ ምስል