በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የተፈቱት የወልቂጤዎቹ  ሙስሊም ወንድሞች በወልቂጤ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 1/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው  መሰረት ከእስር የተፈቱት ሙስሊም ወንድሞች በወልቂጤ ከተማ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው ወንድሞች መካከል የመዝገቡ ተጠሪ ወንድም ኤልያስ ከድርን ጨምሮ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩ 8 ወንድሞች  ከእስር መፈታታቸው  የሚታወስ ሲሆን ከወልቂጤ ከተማ ታስረው የነበሩት ወንድሞች ወደ መኖሪያቸው ወልቂጤ ከተማ ሲመለሱ ከፍተኛ የሆነ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው  ተዘግቧል፡፡

የከተማው ህዝብ ሙስሊም  በዕለቱ በአደባባይ በመውጣትና በመስጂድ በመገኘት አሁንም የጀግኖቻችን አጋር መሆኑን ግልፅ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን  ከእስር የተፈቱት ወንድሞችም በወልቂጤ በታላቁ ረቢዕ መስጂድ በመገኘት ከናፈቃቸው ህዝበ ሙስሊም ጋር ተገናኝተዋል፡፡

 በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይም ከእስር የተፈታው  ወንድም ሙዓዝ ሙደሲር በታላቁ ረቢዕ መስጂድ ንግግር ያደረገ ሲሆን  " እጅግ በርካታ መብታቸውን የጠየቁ ሙስሊም ታሳሪዎች በእስር ባሉበት ሁኔታ ደስታችን ሙሉ አይሆንም" በእስር ቆይታችን ወቅት ከኛ እና  ከቤተሰባች ጎን በመሆን አጋርነቱን ሲያሳይ ለቆየው ህዝብ ምስጋናዬን አቀርባለው ሲል ምስጋናውንማቅሩ ተዘግቧል፡፡

የተፈቱትን ወንድሞች በአዲስ አበባ እና በወልቂጤ ላይ  ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የታሳሪ ቤተሰቦች በግል እና በጀምዓ በመሆን የተፈቱትን እየዘየሩ መሆኑ ታውቀዋል፡፡

ከወልቂጤ ከተማ ሙስሊም ጀምዓዎች በተጨማሪ እድሜ እና ሃይማኖት ሳይገድባቸው  ታዳጊ ህፃናት ፣ወጣቶች ፣አባቶች፣ እናቶች የአከባቢ ሽማግሌዎች እና  ቤተ ዘመድ  የተፈቱትን ወንድሞች እንኳን አላህ በሰላም ከቤተሰባችሁ ጋር ቀላቀላችሁ ለማለት ወደ ተፈቱት ቤተሰቦች ቤት ለዚያራ እየጎረፉ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

ከሙስሊሙ በተጨማሪም የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ የወልቂጤ ነዋሪዎች የተፈቱትን ወንድሞች እየዘየሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

 ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው ለእስር ከተዳረጉት ሙስሊም ወንድሞች መካከል ሶስት የሚሆኑት አሁንም ድረስ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት  በእስር ላይ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን የተፈረደባቸው የእስራት ጊዜ ከ 12 ቀናት ቡኋላ የሚጠናቀቅ በመሆኑ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልፆል፡፡

እነዚህም ሶስት ወንድሞች  ጃአፈር ዲጋ ፣ወንድም ፋሩቅ ሰኢድ እና  ወንድም አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የነበረው የመዝገቡ ተጠሪ ወንድም ኤልያስ ከድርም ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ እና በናፈቀው ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር የተቀላቀለ ሲሆን በርካቶች ወደመኖሪያ ቤቱ በመሄድ እየዘየሩት እንደሚገኙ ታውቃል፡፡

ተጨማሪ ምስል