በኢትዬጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊገነባ ለታቀደው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የተጠራው ስብሰባ በአህባሽ መራሹ መጅሊስ እንዲታገግ መደረጉ ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 15/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በኢትዬጲያ የመጀመሪያ የሆነ ግዙፍ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲለማስገንባት የተጀመረውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በዛሬው እል እሁድ የተጠራውን ስብሰባ አህባሽ መራሹ ህገ ወጥ መጅሊስ ከፌደራልፖሊስ ጋር በመተባበር ስብሰባው እንዳይካሄድ ማሳገዱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች  ዘግበዋል፡፡

ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች ትልቅ ባለውለታ በሆኑት በሃጂመሐመድ አወል ረጃ ስም የተሰየመው ይህ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ በዘመናዊ መልኩ ህዝበ ሙስሊሙን ዲናዊ እውቀትን ለማስጨበት  አቅዶ የነበረ  ሲሆን ኢስላማዊ እውቀትን ለመቀሰም ብዙ መከራዎችን የሚያስተናግዱ ሙስሊሞችን የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ ይህን ዘመናዊ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደነበር ታውቋል፡፡

ሊገነባ የታሰበው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ የነበረ ሲሆን በውስጡም 1200ካሬ.ሜ ላይ ያረፈ ዘመናዊ መስጂድ አብሮት እንደሚገነባ ተገልፆ ነበር፡፡

የዚህ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቱ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ ወደ ተግባር ለመውረድ እንቅስቃሴዎች እየተደረገ የነበረ ሲሆን የዚህ እንቅስቃሴ አካል የነበረው በዛሬው እለት እሁድ ሚያዚያ 15 በአዲስ አበባ ከተማ በጦር ሃይሎች በኢሞ ታወር ህንፃ አዳራሽ የተጠራው ስብሰባ በአህባሽ መራሹ መጅሊስ እንዲደናቀፍ መደረጉ ታውቋል፡፡

የስብሰባ አዳራሹን በፌደራል ፖሊሶች እንዲከበብ በማድረግ ሙስሊሙ በፕሮግራሙ ላይ እንዳይካፈሉ ያገዱት ሲሆን መጅሊሱ ዘወትር የሙስሊሙን ገንዘብ ከመዝረፍ እና ግላዊ ጥቅማቸውን ከማሳደድ ውጪ ሙስሊሙ በዲናዊም ሆነ በሃገራዊ ልማት ላይ እንዳይሳተፍ ዘወትር እንቅፋት መሆናቸውን መቀጠላቸው ተዘግቧል፡፡

አህባሽ መራሹ ህገ ወጡ መጅሊስ መስጂዶችን ከሙስሊሙ መንጠቅ፣መድረሳዎችን ማዘጋት፣የዳዕዋ ፕሮግራሞችን ማሳገድ፣ኢስላማዊ እንቅስቃሴዎችን ማስቆም፣ኡለሞች ደረሶችን እንዳያስቀሩ ከመስጂድ ማባረር  የዘወትር ስራው ሲሆን የህዝቡን ገንዘብ ለግላዊ ጥቅማቸው ከማዋል በተጨማሪ አመቱን ሙሉ መውሊድ ልናከብር ነው በሚል በየመስጂዱ በጫት ሰክረው በመጨፈር፣የመስጂድንክብር ከማዋረድ አልፈው በየቦታው የቀብር አምልኮዎች እንዲስፋፉ ትምህር በመስጠት ላይ መጠመዳቸው ይታወቃል፡፡

የተለያዩ እምነቶች የራሳቸው የሆነ ሃይማኖታዊ ኮሌጆች ያሏቸው ሲሆን የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ግን እስካሁን አንድም ኮሌጅ ሳይኖራቸው ለዘመናት መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ይህን አሳዛኝ ታሪክ ለመቀየር ሙስሊሙ እንቅስቃሴ በጀመረበት  በዚህ ወቅት የሙስሊሙ ተወካይ ነን በሚል በመንግስት የተሾሙት ፅንፈኛ የአህባሽ አመራሮች ከጅምሩ እቅዱ እንዳይሳካ የለመዱትን እገዳ እና ክልከላ ተግባራዊ ማድረግ መቀጠላቸው ተዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል