በአፋር ክልል ታዋዊ አሊም እና ዳዒ የነበሩት ኡስታዝ አብዱቃድር ለአድ ሙሀመድ ወደ አኼራ መሄዳቸው ተዘገበ
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
ፍትህ ራዲዬ/ ታህሳስ 30/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአፋር ክልል በሚገኙ ከተሞች በየመስጂዱ በመሄድ ዳዕወ በማድረግ እና ኡማውን በማገልገል ተወዳጅነትን እና ተቀባይነትን ያተረፉት ኡስታዝ አብዱቃድር ለአድ ሙሀመድ ወደ አሄራ መሄዳቸውን የአፋክ ክልል ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ኡስታዝ አብዱቃድር ለአድ ሙሀመድ በአፋር ክልል እየዞሩ ለሙስሊም ማህበረሰብ ደእዋ እያደረጉ መስጅድ መኖሪያ አድርገው ኡማውን በህይወት ዘመናቸው ሲያገለግሉ የቆዩ ታላቅ አሊም መሆናቸው ተገልፆል፡፡
ኡስታዝ አብዱቃድር በየመስጅዶች የሚታወቁበት ልዩ ቅላፄ ያለው ረጋ ባለድምፅ በሚያደረጉት አዛን የመስጅድ ጀማአዎች ለይተው ያውቁት የነበረ ሲሆን ወደ ተለያዩ ክፍለ ሀገራት ወጣ በማለት በየመስጅዶች ይዞሩ እንደነበር ተዘግቧል፡፡
: በተለይ በአዲስ አበባ በአንዋር መስጅድ ለበርካታ አመታት የሱብሂ ሰሏት አዛን በማድረግ የሚታወቁ የነበሩ ሲሆን ለዱንያ ህይወት ምንም ቦታ የማይሠጡ ዛሂድ የሆነ አሊም እንደነበሩ በቅርበት የሚያውቋቸው ሙስሊሞች ገልፀዋል፡፡
አብዛኛውን ጊዜያቸውን በመስጂድ ውስጥ ቁርአን በመቅራት የሚያሳልፉ የነበሩ ሲሆኑ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ ብቻ የሚቆይ ስሜት ኮርኳሪ ዳዕዋ እንባቸውን እያረገፉ ዳዕዋ በማድረግ የሚታወቁ አሊም ነበሩ፡፡
በአፋር ክልል ታዋቂ የነበሩት እኚህ አሊም አላህን በመገዛት ላይ እና ኡማውን በማገልገል ለረጅም አመታት ከቆዩ ቡሃላ በትላንትናው እለት ቅዳሜ በአፋር ዱብቲ ከተማ ህይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል፡፡
በኚህ ታላቅ አሊም ሞት የአፋር ሙስሊሞች ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ መውደቃቸው የተዘገበ ሲሆን ከፍተኛው ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም እና ታላላቅ አሊሞች በተገኙበት ስርአት ቀብራቸው መፈፀሙን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
አላህ ማረፊያቸውን ዘነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው

ተጨማሪ ምስል