በአዳማ ከተማ በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች የሰርግ ስነ ስርአት ላይ ቅዱስ ቁርአን ተቀዳዶ መገኘቱ ተዘገበ
ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 30/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በአንድ የሰርግ ስነ ስርአት ላይ ቅዱስ ቁርአን ተቀዳዶ መሬት ላይ ተበትኖ መገኘቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
ቅዱስ ቁርአኑ ተቀዳዶ የተገኘው በአዳማ ከተማ በቁባ መስጂድ አካባቢ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህ ተግባር የተፈፀመውም በአንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች የሰርግ ስነ ስርአት ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
በርካታ የቁርአን ገፆች ተቀዳደው መሬቱ ላይ ተበትነው የተገኘ ሲሆን የሰርግ ስነ ስርአትን ለማድመቅ በሚል መሬት ላይ ከሚበተነው ወረቀቶች ጋር አብሮ መበተኑ ታውቋል፡:
ይህን ድርጊት ሆን ብለው የፈፀሙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተሰማ ሲሆን ድርጊቱ ሙስሊሙ ማህበረሰብን ማስቆጣቱ ታውቋል፡፡
ለሰርግ ስነ ስርአት ማድመቂያ በሚል ወረቀቶች ተቀዳደው መሬት ላይ እንደሚበተኑ የሚታወቅ ሲሆን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬችም ቅዱስ ቁርአንን በብዛት በመቀዳደድ መሬት ላይ እንዲበተን በማደረግ በሰዎች በጫማ እንዲረጋገጥ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡
የዚህ መሰሉ ቁርአንን የመቀዳድ፣የማቃጠል እና ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎት የማዋል ተግባር በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች ዘንድ በብዛት እንደሚፈፀም የሚታወቅ ሲሆን በጅማ ከተማ በተከሰተው የሃይማኖት ግጭትም ዋነኛ መነሻ ምክንያት የነበረው በአንድ የፕሮቴስታንት የእምነት ተቋም ውስጥ ቁርአንን ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎት እንዲውል መፀዳጃ ቤት በር ላይ እንደ ሶፍት በመንጠልጠሉ መሆኑ ይታወሳል፡፤
በዩኒቨርሲቲዎች እና በትምህርት ተቋማት ውስጥ ቅዱስ ቁርአንን ማቃጠል እና ቀዳዶ መጣል በተደጋጋሚ የሚፈፀም ተግባር ሲሆን ይህን ተግባር ሲፈፅሙ የሚገኙ ተማሪዎች የተወሰነ ጊዜ ብቻ ተቀጥተው ወደ ትምህርታቸው እንደሚመለሱ ይታወቃል፡፡
የአክፍሮት ሃይላት በሙስሊሙ ላይ የሚያደርጉት ትንኮሳ ተባብሶ በአሁኑ ወቅት የቀጠለ ሲሆን በስልጤ ዞንም ከመንዙማ በተጨማሪ በባህላዊ ዘፈኖች ጭምር መዝሙሮችን በማዘጋጀት ለህዝቡ እየበተኑ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወቃል፡፡
ከአንድ ወር ወዲህ እስከ 25 የሚደርሱ በስልጥኛ የዘፈን ስልት የተቀናበሩ የስልጥኛ መዝሙሮችን በሚሞሪ እና በተለያዩ ዘዴዎች ወደ ህዝቡ ማሰራጨታቸውን የዞኑ ተወላጆች አስታውቀዋል፡፡
በተለይ በስልጢ እና ዳሎቻ ወረዳ ላይ ሙስሊሙ ባለማወቅ በሰርግ ስነ ስርአት ላይ ሁሉ ዘፈን መስሏቸው መዝሙሩን ሲከፍቱ እ ናሲያደምጡ እንደነበር ታውቋል፡፤
የአክፍሮት ሃይላት ከኬኒያ የሚተላለፍ የስልጥኛ የሰበካ ራዲዬ ጣብያም በመክፈት ሙስሊሙን ለማክፈር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በዘፈን እና በመንዙማም አስመስሎ መዝሙሮችን በማዘጋጀት ሙስሊሙን ከዲኑ ለማስወጣት ጠንክረው እየሰሩ መሆናቸው ተዘግቧል፡፤
ተቀዳደው የተገኙት የቁርአን ምስሎች እንደደረሱን የምናቀርብ ሲሆን ከዚህ በታች ከዜናው ጋር አባሪ ተደርጎ የተለጠፈው በአዳማ ከተማ የተቀዳደደ አለመሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን

ሃስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል

ተጨማሪ ምስል