በአዲስ አበባ የሚገኘውን የአሊፍ መስጂድን ለመታደግ በተደረገው ርብርብ የሚፈለገው የገንዘብ መጠን መገኘቱ ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ መጋቢት 24/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአዲስ አበባ በኡራኤል እና ባምቢስ አካባቢ የሚገኘው አሊፍ መስጂድ ቦታውን ባለቤቶቹ ለመሸጥ በማሰባቸው ምክንያት መስጂዱን በመስጂድነት ለማስቀጠል በተደረገው ርብርብ የመስጂዱን ቦታ ለመግዛት የተጠየቀው ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ መሟላቱን አስተባባሪዎቹ አስታውቋል፡፡
መስጂዱ በአቅም እጥረት ምክንያት መዘጋቱን የአካባቢው ሙስሊሞች መግለፃቸው የሚታወቅ ሲሆን መስጂን በመስጂድነት ለማስቀጠል ቤቱን ለመግዛት በተደረገው ጥረት ሙሉ ወጪው በህዝበ ሙስሊሙ መዋጮ ሊሸፈን መቻሉ ተዘግቧል፡፡
አሊፍ መስጂድ የግል መኖሪያ ቤትን በክራይነትን በመጠቀም ለረጅም አመታት ሙስሊሙን ማህበረሰብ ሲያገለግል የቆየ ሲሆን በርካታ ህፃናትም ቁርአን ሲቀሩበት እና ሲማሩበት የነበረ መስጂድ መሆኑ ይታወቃ፤፡፡
ይህን መስጂድ ያከራዩት ግለሰቦች ቤቱን መሸጥ በመፈለጋቸው እና መስጂዱን ለመግዛትን የአካባቢው ሙስሊሞች አቅም ስላጠራቸው መስጂዱ መዘጋቱ ይታወቃል
ይህ መስጂድ ለ 15 አመታት ያህል ሙስሊሙ ሲጠቀምበት የቆየ ሲሆን መስጂዱ ባለቤት ይዞታ እንዲቀጥል ለመስጂዱ አከራዬች የቤቱን ሽያጭ ሙሉ ገንዘብ በመክፈል መስጂዱን በድጋሚ ማስቀጠል የሚቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱ ተገልፆል፡፡
ይህን ተክትሎ መስጂዱን ለመግዛት 4.5ሚሊዬን ብር የተጠየቀ ሲሆን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ርብርብ የተጠየቀው ሙሉ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል፡፡
የመስጂዱ ቦታ ባለቤቶች ሙሉውን ክፍያ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ካላጠናቀቁ ለሌላ አካል ቦታውን አሳልፈው እንደሚሰጡት ገነ ገደብ አስቀምጠው የነበረ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያዎች በተካሄደ ቅስቀሳ በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ የሚገኘው ሙስሊም ማህበረሰብ በመረባረብ የተጠየቀውን ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉ ተገልፆል፡፡
መስጂዱን ለመግዛት የተጠየቀው ገንዘብ ቢሟላም የመስጂዱ ቦታ ባለቤት ከሃገር ውጪ በመሆኗ ክፍየውን የመፈጸም እና ርክክብር የማካሄዱ ሂደት ባለቤቷ እስክትመጣ እየተጠበቀ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል፡፡
መላው ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይም በአረብ ሃገራት የሚገኙ እህቶች እና ወንድሞች ላደረጉት ታላቅ አስተዋፅኦ አስተባባሪዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ገንዘቡን ለማሰባሰብ በተደረገው ዘመቻ ላይ የተሳተፉትን ሁሉ አስተባባሪዎቹ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ተጨማሪ ምስል