በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የሞባይል ኢተርኔት ለ 2ኛ ቀን በመንግስት እንደተዘጉ መሆኑ ታወቀ

ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 26/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

መንግስት በቢሾፍቱ  የኢሬቻ በኣል ለማክበር በተሰበሰቡ በሚሊዬን በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ የሃይል እርምጃ በመውሰድ በንፁሃን ላይ  ባደረሰው  ግድያ ከፍተኛ ቁጣ በህዝቡ ዘንድ በመቀስቀሱ  የሰጋው መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ዋና ከተማ አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ ተቃውሞ በህዝቡ መሃል በመቀስቀሱ መረጃ ለህዝቡ እንዳይዳረስ ለማፈን በሚል ከትላንት እሮብ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ  ታውቋል፡፡

ዛሬ ለሁለተኛ ቀን  የሞባይል ኢንተርኔት ተዘግቶ የዋለ ሲሆን  የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጥ የህዝቡን ቁጣ እና ተቃውሞ ለማቀዛቀዝ መንግስት እየጣረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎት ቢቋረጥም በተለያዩ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ከተሞች ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃወሞ እየተካሄደ መሆኑ የተዘገበ ሲሆን የመንግስት ታጣቂ ሃይሎችም ወደ ህዝቡ በመተኮስ ዜጎችን እየገደሉ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በጅማ ፣በሃዋሳ እና በአዳማ ዩኒቨርሰቲ የሚገኙ ተማሪዎችም ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸው የታወቀ ሲሆን  በጅማ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የኦሮሚያ እና የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች በጋራ ትግላቸውን ለማድረግ መወያየታቸውን እና መስማማታቸው ተዘግቧል፡፡

መንግስት አሁንም የሃይል እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን በትላንትናው እለት ያስታወቀ ሲሆን ህዝባዊ ተቃውሞውን ከግብጽ ድጋፍ የሚደረግለት ነው በማለት የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት እየሞከረ መሆኑ ታውቋል፡፡

በመንግስት የተለቀቀው ቪዲዬ በ2014 ኤፕሪል ወር ላይ  የኦሮሞ ሰማእታትን ቀን ለማክበር  በማሰብ በካይሮ የሚገኙ ስደተኞች ካይሮ አረብ መዓዲ በሚባል ሰፈር በሚገኝ እሰታዲየም ውስጥ በተካሄደው  ዝግጅት ላይ  የተቀረፀ መሆኑን የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡

በዚህ ዝግጅት ላይ በግብፅ ውስጥ የሚገኙ ስደተኛውን የሚረዱ አላም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች እና ሎካል የሆኑ የግብፅ ሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች  በተጋባዥነት ተካፍለው እንደነበር የተገለፀ ሲሆን እነዚህ እንግዶችም በዝግጅቱ ላይ ንግግር በማድረግ ለስደተኛው ከጎናቸው መሆናቸው የተናገሩበት መሆኑን በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች አስታውቋል፡፡

በመድረኩ ላይ ተጋብዘው የተናገሩት የግብፅ የሰብአዊ መብት ተማጓች ግለሰቦች በግብፅ መንግስት ሊደገፉ ይቅርና በግብፅ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በግብፅ መንግስት በኩል ባለባቸው ጫና ለደህንነታቸው የሚሰጉ መሆናቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡

የኢትዬጲያ መንግስት በህዝቡ የተነሳበትን ተቃውሞ አቅጣጫ ለማስቀየስ የዛሬ 2 አመት የተካሄደን ፕሮግራም አሁን እንደተደረገ አስመስሎ በማቅረብ  ህዝባዊ ተቃውሞው ከግብጽ መንግስት ድጋፍ የሚደረግለት እንደሆነ በማስመሰል የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት እየተፍጨረጨረ መሆኑ ተገልፆል፡፡

በኢትዬጲያ መንግስት የቀረበውን ውንጀላ የግብፅ መንግስት ያጣጣለው ሲሆን በኢትዬጲያ እየተካሄደው ባለው ተቃውሞ  የግብፅ መንግስት ምንም ንክኪ እንደሌለው ማስታወቁን  ሲሲ ቲቪ ዘግቧል፡፡

የግብፅ  መንግስ የኢትዬጲያን ሰለም እና  መረጋጋት  እንደሚፈልግ ያስታወቀ ሲሆን በተፈጠረው ረብሻ እጁ አለበት መባሉን ማስተባበሉን  ሲሲቲቪ ዘግቧል፡፡