ሰበር ዜና!!!

አርብ የካቲት 11/2008

ዛሬ የካቲት 11/2008 በአንዋር መስጂድ ከጁሙዓ መልስ የድምጽ ተቃውሞ ተካሄደ! ባለፈው ሳምንት ከተደረገው የጽሁፍ መፈክር የማሳየት ተቃውሞ በኋላ መንግስት ወደመስጊዱ የሚመጣውን ሰው በፍተሻ ሲያጉላላ የነበረ ቢሆንም የድምጽ መፈክሮች በድምቀት ተሰምተዋል!

ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ብሄራዊ ጭቆናው እስኪገታ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም በተደጋጋሚ ሲገልጽ የቆየ ሲሆን በዛሬው ተቃውሞውም ‹‹ብሄራዊ ጭቆናው ይብቃ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!››፣ ‹‹መንግስት የለም ወይ?›› በሚሉ መፈክሮቹ ቁርጠኝነቱን እና የትግል ወኔውን ገልጿል!

ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!

ምስል