በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ በውርጌሳ እና በመርሳ ከተማ ህገ ወጡ መጅሊሶች መስጂዶች እንዳይታደሱ እና እንዳይሰሩ እያገዱ መሆናቸው ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 24/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በውርጌሳ ከተማ የሚገኘውን የአቡበከር መስጂድን በአዲስ መልኩ ለማሰራት የታሰበውን እቅድ ህገ ወጡ መጅሊስ እንዲታገድ ማድረጉን ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
ይህ መስጂድ ከተገነባ 20 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ለአካባቢው ሙስሊሞች በበቂ ሁኔታ እንዲገለገሉበት ለማስቻል መስጂዱን ዳግም ለማስገንባት የተደረገው እንቅስቀሴ በአህባሽ መራሹ መጅሊስ እንዲታገድ መደረጉ ታውቋል፡፡
በመስጂዱ በአፍሪካ ቲቪ በጄሉ መልቲ ሚዲያ አማካኝነት ቀረፃ ተደርጎለት በሃላል መዝናኛ ፕሮግራም ተሰርቶለት መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን መስጂዱን ለማስገንባት ለቀረበው ጥሪም ሙስሊሙ ትልቅ ተነሳሽነት ቢያሳይህም ህገ ወጡ መጅሊሶች ግ መስጂዱ እንዳይገነባ እገዳ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡
መስጂዱ በጁምዓ ቀን እና በረመዳን ወር ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝበ ሙስሊም የማያስተናግድ በመሆኑ ከመስጂዱ በር ፊት ለፊት አስፋልት ላይ በፀሃይ እየተቃጠሉ እና በዝናብ ወቅትም ዝናብ እየመታቸው ሙስሊሙ ለመስገድ እንደሚገደድ ታውቋል፡፡
ይህን ችግር ለመቅረፍም የመስጂዱን በረንዳ በ 130 ቆርቆር ጣሪያ ለማልበስ እቅድ ተይዞ እንቅስቃሴ ቢጀመርም ይህንንም እንቅስቃሴ ህገ ወጡ መጅሊሶች ለማሳገድ ጥረት አድርገው እንደነበር ተሰምቷል፡፡
ለመስጂዱ በረንዳ ጣሪያ ማሰሪያ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በጁምዓ ቀን ለማካሄድ በታሰበበት ቀን ህገ ወጡ መጅሊሶች በጠዋት ወደ መስጂዱ በመሄድ የገቢ ማሰባሰቢያው እንዳይካሄድ ለማጨናገፍ የሞከሩ ቢሆንም የመስጂዱ ወጣት ጀምዓዎች በቁርጠኝነት እንቅስቃሴያቸውን በመቀጠል በእለቱ የተለያዩ ቁሳቁሶች እና 50ሺህ ብር መሰብሰብ መቻላቸው ተዘግቧል፡፡
ከመስጂዱ በረንዳ ጣሪያ በተጨማሪም መስጂዱን ለማሳደግም ወደፊት ተባብረው ለማሰራት ተነሳሽነት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን ወደፊትም መስጂዱን ለማስገንባት ቃል በመጋባታቸው ተዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ ዜናም በሰሜን ወሎ ዞን በመርሳ ከተማ ልዩ ቦታው አብዬት ፉሪ መስጂድ የሚባለውን መስጂድ ለማሰራት የታቀደው እንቅስቃሴ በህገ ወጡ መጅሊስ እንዲታደግ መደረጉ ታውቋል፡፡
መስጂዱን ለማስገንባት በቅርቡ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለማካሄድ እቅድ ከተያዘ ቡሃላ ህገ ወጡ መጅሊስ እንዳይካሄድ እገዳ መጣላቸው ተዘግበዋል፡፡
በቅርቡ በሃብሩ ወረዳ በሊብሶ ከተማ እንደተደረገው ኡስታዞች እና ኡለሞችን በመጋበዝ ታላቅ ፕሮግራም ለመስጂዱ ግንባታ ለማዘጋጀት ቢታቀድም መስጂዶችን በመቀማት እና በማዳከም ላይ የሚገኙት አህባሾች ይህ ፕሮግራምም እንዳይካሄድ ማገዳቸውን የአካባቢው ሙስሊሞች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
ህገ ወጡ የፌደራል መጅሊስ በሐረር ከተማ አቦይ ስብሃትን ጨምሮ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስተር የሆኔትን ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ፣የሐረሪ ክልል ፕሬዝደንትን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተካፈሉበት ጉባኤ ለሶስት ቀናት ያካሄዱ ሲሆን በየቦታው ለመስጂድ ግንባታ ተብሎ እየተካሄደ የሚገኘውን ታላላቅ ፕሮግራሞች የአክራሪዎች እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ነው በሚል ባስቸኳይ እንዲቆም ጠንክረው እንደሚሰሩ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ምስል