በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት  የደሴ ወጣቶች ከ3 አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተበየናቸው

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 18/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በደሴ ከተማ ከ 3 አመት በፊት በመንግስት ደህንነቶች አቀናባሪነት የተገደሉትን ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል ሰበብ እና በሽብር ተግባ ላይ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከደሴ ከተማ ለእስር የተዳረጉት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ የሚገኙት  13 ወጣት ሙስሊሞች  የቅጣት ውሳኔያቸውን ለመስማት በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት በዛሬው እለት  ጥር 18  የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በታህሳስ 27 በነበራቸው ችሎት በ13ቱም ተከሳሾች ላይ  ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ብይን ያስተላለፈ ሲሆን አቃቤ ህጉ እና ተከሳሾች የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያቸውን ለፍ/ቤቱ እንዲያቀርቡ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት በሁሉም ታሳሪዎች ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈ ሲሆን ከ 3አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት ፅኑ እስራት እንደበየነባቸው ተዘግቧል፡፡

አስራ ሶስቱ ተከሳሾች በሶስት ደረጃ ተከፍለው በተለያዩ አንቀፆች ጥፋተኛ መባላቸው የሚታወስ ሲሆን  በዚህም መሰረት ጥፋተኛ በተባሉበት አንቀፅ የቅጣት ብይን እንደተላለፈባቸው ታውቋል፡፡

በዚህም 8ኛ ተከሳሽን በ16 አመት ፅኑ እስራት፣ 1ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ እና በ15 እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽን በ15 አመት ከ6 ወር፣ 6ኛ እና 11ኛ ተከሳሾችን ደግሞ በ14 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ተዘግቧል

2ኛ ተከሳሽን ደግሞ በ12 አመት ፅኑ እስራት፣ 5ኛ እና 12ኛ ተከሳሾች ደግሞ በ6 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል።

ከዚህ ባለፈም 10ኛ ተከሳሽ በ5 አመት፣ 14ኛ ተከሳሽ 4 አመት ከ4 ወር እንዲሁም 13ኛ ተከሳሽን ደግሞ 3 አመት ከ8 ወር እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉ ተገልፆል

1. አህመድ ኢድሪስ  15 አመት

2. አንዋር ኡመር ሰዒድ 12 አመት

3. ሷሊህ መሀመድ አብዱ15 አመት

4. አደም አራጋው አህመድ 15 አመት

5. አብዱራህማን እሸቱ መሀመድ 6 አመት

6. ኢብራሒም ሙሔ ይማም 14 አመት

7. ዑመር ሁሴን አህመድ 15 አመት ከ6 ወር

8. ይመር ሁሴን ሞላ 16 አመት

10. እስማኤል ሀሰን ይመር 5 አመት

11. ከማል ሁሴን አህመድ 14 አመት

12. አብዱ ሀሰን መሀመድ 6 አመት

13. አህመድ ጀማል ሰይድ 3 አመት ከ 8 ወራት

14. ሙሀመድ ዩሱፍ መሀመድ 4አመት ከ 4 ወር ፅኑ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡

የችሎቱ ዳኛ የቅታት ውሳኔውን ሲያነቡ  ወንድሞቻችን በተክቢራ እና በፈገግታ ውሳኔውን ሲቀበሉ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ሃስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት  የደሴ ወጣቶች ከ3 አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተበየናቸው

ተጨማሪ ምስል