በነብዩ ሲራጅ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈባቸው

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር 27/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች ለእስር የተዳረጉት በነብዩ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 27 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኮሚቴውን በሃይል ለማስፈታትን እና ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገብቷል ብላቹሃል በሚል በሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህጉን ምስክሮች በመስማት ጉዳዩን ከመረመረ ቡኋላ በሁሉም ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዳስተላለፈባቸው የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ሆናችሁ አግኝቻቹሃለው በሚል እንዲከላከሉ የበየነባቸው ሲሆን ፍትህ በሌለበት ሃገር መከላከያ ማቅረብ ጥቅም የለውም በሚል አንከላከልም የሚል ውሳኔያቸውን ለፍርድ ቤቱ አሳውቀዋል፡፡

የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው 7ቱ ሙስሊሞች

1. ነብዩ ሲራጅ

2. ሰፋ በደዊ

3. መሃመድ ሰዒድ

4. ሰላሃዲን ከድር

5. ሙጂብ አደም እረሺድ

6. ከድር ታደለ

7. አህመድ ኡመር መሆናቸው ታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱም በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል የሚጣልባቸውን የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለታህሳስ 24 ቀነ ቀጠሮ መስጠቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡