በነብዩ ሲራጅ መዝገብ  የተከሰሱት   7 ሙስሊም ወንድሞች ከ 3 አመት ከ 3 ወር እስከ 3 አመት ከ9 ወር የሚደርስ ፅኑ  እስራት ቅጣት ተበየነባቸው
 

ፍትህ ራዲዬ/ታህሳስ 27/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች ለእስር የተዳረጉት በነብዩ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች    በታህሳስ 24    የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት  14ኛው ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ብይን እንዳስተላለፈባቸው የመታወስ ሲሆን በዛሬው እለትም የቅጣት ውሳኔያቸውን ለማድመጥ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር  የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኮሚቴውን በሃይል ለማስፈታትን እና  ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገብቷል ብላቹሃል በሚል በሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህጉን ምስክሮች በመስማት ጉዳዩን ከመረመረ ቡኋላ ሁሉም ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያቸውን ለፍርድ ቤቱ እንዲያስገቡ በህዳር 24 ትዕዛዝ መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው  ችሎትም  ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ማስተላለፉ ተዘግቧል፡፡

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ከተከሰሱት 7 ሙስሊም ወንድሞች መካከል በስድስቱ ላይ  የ3 አመት ከ11ወር እስራት ቅጣት የበየነ ሲሆን  በሁለተኛ ተከሳሽ በሆነው በሰፋ በደዊ ላይ  ደግሞ  የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ብይን ማስተላለፉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ተከሳሾቹ ችሎት በቀረቡበት ወቅት የፍርድ ቤቱን ኢ ፍትሃዊነት እና የታሰሩበትን አላማ በቆራጥነት እንደሚገፉበት ያመላከተ ተቃውሞ በችሎቱ ውስጥ ድምፃቸውን ከፍ አድረገው ማሰማታቸው ተዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ወንጀል የተከሰሱት በከድር መሐመድ የክስ መዝገብ የሚገኙት  19 ሙስሊም ወንድሞችም የ 5 አመት ከ6 ወራት በታህሳስ 25/2009 እንደተበየነባቸው የሚታወስ ሲሆን ጋዜጠኛ ራሰማ ሶሪ ብቻ  በሽተኛ መሆኑን ባቀረበው የቅጣት ማቅለኛ 4 አመት ከ 5 ወራት እስራት እንዲቀጣ እንደተበየነበት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ምስል