በትግራይ ክልል በኹኩፍቶ ወረዳ ቀንደኛ የአህባሽ አቀንቃኞች የሙስሊሙን ገንዘብ መመዝበራቸው ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር18/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በርካታ ሙስሊሞች በሚኖሩበት ኹኩፍቶ በተባለው አካባቢ ለሙስሊሙ ትምህርት ቤት ማሰሪያ በሚል የተሰበሰበውን ገንዘብ የወረዳው የአህባሽ አቀንቃኞች መመዝበረቸውን የአካባቢው ተወላጆች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

ኹኩፍቶ በትግራይ ደቡባዊ ዞን ያለ ሙስሊም ማህበረሰብ የሚበዛበት ኣከባቢ ሲሆን በርካታ ታላላቅ አሊሞችን ያፈራ ቦታ እንደነበር ተገልፆል፡፡

የአህባሽ አስተሳሰብ በግዳጅ በመንግስት አማካኝነት ሲጫን በትግራይ ክልል በአህባሾች ሰለባ እንዲሆን ከተደረገው መካከል ይህ አካባቢ ተጠቃሽ ሲሆን አቶ ኢድሪስ ጀማል የተባለው የቀድሞ የህወሃት ታጋይ እና የአህባሽ አቀንቃኝ የሆነው ግለሰብ የሙስሊሙን ገንዘብ እየመዘበረ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡

አቶ ኢድሪስ በአካባቢው ሼህ አብዱልአዚዝ ከሚባል ሰው ጋርበመተባበር በሙስሊሙ ላይ ከፍተና በደል እና ግፍ እየፈፀሙ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በራያ የታሰሩት በርካታ ኡለሞች እንዲታሰሩ ዋነኝ ምክንያት መሆኑም ተገልፆል፡፡

በሼህ አብዱልመናን መዝገብ ተከሰው በግፍ እስራት ላይ የሚገኙት ኡለሞች እና ኡስታዞችም በዚህ አቶ ኢድሪስ በተባለ ግለሰብ ጠንሳሽነት ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ኩኩፍቶ እና ሂጅራ ወራዳዎች ሙሉ በሙሉ ሙስሊሞች የሚኖርባቸው ቦታዎች ሲሆን በነዚህ ወረዳዎች ላይ ትምህርት ቤት እናሰግነባለን በሚል ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰቡን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ይህን ገንዘብ ትምህርት ቤት ለማስገንባት በሚል ከህዝቡ ቢሰበሰብም አቶ ኢድሪስ የተባለው ግለሰብ በግሉ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ገንዘቡን በማስገባት የግል መኖሪያ ቤት እና ቁሳቁስ እንደገዛበት የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡

ይህን ከፍተኛ ገንብ በተሰባሰበበት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይም አቶ ኢድሪስ የተባለው ግለሰብ ከራያ ቢራ ፋብሪካ ሁለት ትልልቅ የጭነት መኪና ሙሉ ቢራ በማስመጣት በፕሮግራሙ የተካፈለውን ህዝብ በአስካሪ መጠጥ መበከሉ ተሰምቷል፡፡

ይህ ቀንደኛ የአህባሽ ሰባኪ እና የቀድሞ የህወሃት ታጋይ የሆነው ኢድሪስ የተባለው ግለሰብ ከህዝቡ ትምህርት ቤት ይገነባል በሚል ገንዘብ ቢያሰባስብም ተማሪዎች በባዶ ሜዳ ላይ ካሮራ ዛፍ ጥላ ስር በመሆን እንዲማሩ እያደረገ ሲሆን ዳስ በቅርቡ ይሰራላቹሃል በሚል ተማሪዎችን እያጭበረበረ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡

ይህ ሰው የመንግስትን የአህባሽ አጀንዳ በትግራይ ክልል እያስፈጸሙ ከሚገኙ ሰዎች መካከል አንዱ በመሆኑ እየፈፀመ በሚገኘው ዝርፊያ በመንግስት አካላት ተጠያቂ ሳይሆን የቀረ ሲሆን ነባር ታጋይ እና መረጃ አቀባይ በመሆኑ ከተጠያቂነት ነፃ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በእስር ላይ የሚገኙ ኡለሞችንም ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ የሚገኝ ካድሬ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በርካታ ኸይር ስራዎችን ሲሰሩ የቆዩ ኡለሞችን ዋሃቢያ ናቸው በሚል በግፍ እንዲታሰሩ ማስደረጉ ተዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል