በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ለህዳር 14 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 14/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በራያ አዘቦ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ለእስር የተዳረጉት ኡለሞች እና ኡስታዞች በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ጥቅምት 7 ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ኡለሞቹ እና ኡስታዞቹ በራያ አዘቦ ወረዳ ኩኩፍቶ በተባለ ቦታ የተያዙ ሲሆን ማይጨው በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ከታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች መካከል ከሳኡዲ አረቢያ ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ኡስታዝ አብዱልመናንን ጨምሮ በአፍሪካ ቲቪ የትግርኛ ዳዕዋ በማድረግ የሚታወቀው ኡስታዝ ከድር ሁሴን፣ሼህ አህመድ ዩሱፍ እና ሌሎችም ሙስሊሞች በግፍ ታስረው እየተሰቃዩ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ መዘገቧ ይታወሳል፡፡ አቃቤ ህጉ ካቀረበባቸው ክስ መካከል ቅሬ(እድር) ላይ አትሳተፉም፣ ዋሃቢያ ናችሁ፣ አብደላህ አል ሃረሪን አትቀበሉም፣ልጆች መልምላችሁ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ትልካላችሁ የሚሉን አሳፋሪ የሃሰት ክሶች እንደሚገኙበት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በቀረበባች ሃሰተኛ ክስ ላይም ፍርድ ቤቱ በሰጠው ቀነ ቀጠሮ መሰረት ጥቅምት 7 ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ዳግም ለህዳር 14 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠጡን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ እነዚህ በግፍ የታሰሩ ኡለሞች ከ10 ወራት በላይ በእስር እየተንገላቱ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቀነ ቀጠሮውን በማራዘም ኡለሞቹ በእስር እንዲማቅቁ እያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡