ሰበር ዜና!!!

‹‹ለበደል እጅ አንሰጥም!›› የሚሉ ድምጾች ተጠናክረው ቀጥለዋል!
አርብ የካቲት 25/2008

በቦረና ዞን በምትገኘው ያቤሎ ከተማ ሌሊቱን የግራፊቲ ፅሁፎች ተጽፈው አደሩ! የሕዝቡን ተቃውሞ የሚያሳዩ መፈክሮች እና ጽሁፎች ተበትነው እና በስልክ እንጨቶች ላይ ተለጥፈው ባደሩበት በዚሁ ተቃውሞ የከተማው ደህንነቶች የተደናገጡ ሲሆን መፈክሮቹን በመገንጠል እና በማጥፋት ላይ ተሰማርተው ያረፈዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከተጻፉት መፈክሮች መካከል ‹‹ብሔራው ጭቆና ይብቃ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!››፣ ‹‹የታሰሩት ይፈቱ!››፣ ‹‹ድራማ ይብቃ!››፣ ‹‹የኦሮሞን ህዝብ መግደል ይቁም!››፣ ‹‹አምባገነን ፍርድ አንቀበልም!››፣ ‹‹ህዝብ ያልተቀበለው ማስተር ፕላን ተቀባይነት አይኖረውም!›› እና ‹‹የኢቢሲ ውሸት በቃን!›› የሚሉት ጎልተው የወጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!