በሳኡዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ያለቅጣት ወደሃገራቸው በሰላም እንዲመለሱ የ3ወር የምህረት ጊዜ መሰጠቱ ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ መጋቢት 12/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በሳኡዲ አረቢያ በተለያዩ መንገዶች ወደ ሃገሪቷ የገቡ እና የመኖሪያ ፈቃዳቸው በተለያዩ ምክንያቶች የተበላሹባቸው የውጪ ሃገር ዜጎች ቅጣት ሳይጣልባቸው በሰላም ወደሃገራቸው እንዲመለሱ የ 3 ወር የምህረት ጊዜ መሰጠቱን የሃገሪቷ አልጋ ወራሽ ይፋ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡

የሳውዲ ዓረቢያ አልጋ ወራሽ መሐመድ ብን ናይፍ ከንጉስ ሰልማን ባገኙት ይሁንታ መሰረት ከህገ ወጥ ነዋሪዎች ነፃ የሆነች ሃገር በሚል ሃገራዊ መፈክር   ህገ ወጦችን የማጥራት ዘመቻ ለማካሄድ መሉ ዝግጅት አድርገው መጨረሻቸውን አስታውቋል፡፡

ለሶስት ወራት የተሰጠው የምህረት አዋጅ ዋና አላማው የስራ እና የመኖሪያ ፈቃድን ህግ የመተላለፍ ችግር ማስወገድ፤ድንበርን ማስከበር፤በህገ ወጥነታቸው ምክንያት ቅጣት ለሚገባቸው  የተለያዩ ሃገር ዜጎችን ይቅርታ በማድረግ ያለቅጣት ወደሃገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ መሆኑ ተገልፆል፡፡

አዋጁ እንደሚያትተው ከሆነ ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በህገወጥ ሲኖሩ የነበሩ የተለያዩ ዜጎች ከመጪው ዕሮብ ረጀብ 1/1438 ዓመተ ሂጅራ ወይም ማርች 29/2017 ጀምሮ በ 90 ቀናቶች ውስጥ ጉዳያቸውን ጨርሰው በሰላም ወደሃገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቧል

ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላቶችም በዚህ ጊዜ ውስጥ ሳውዲን ለቀው ለሚወጡ የተለያዩ ሃገር ዜጎዝ ነገሮችን እንዲያመቻቹና እንዲያስተናግዱ ትዕዛዝ መተላለፉ ተዘግቧል፡፡

ይህንን አዋጅ ተከትለው የወጡ ዜጎች በህጋዊ መንገድ ተመልሰው ወደሳውዲ መግባት እንደሚችሉም የተገለፀ ሲሆን አሻራም ሆነ ሌላ ተያያዥ ነገር እንደማይያዝባቸው ተገልፆል፡፡

በወጣው አዋጅ ስር ከሚጠቃለሉ ጉዳዬች መካከል በዑምራ፤በሐጅ፤በዝያራ ወይንም በትራንዚት ቪዛ ወደ ሳዊድ ገብተው ሳይመለሱ የቀሩና የመኖሪያ ፈቃዳቸው (ኢቃማ) በተለያዩ ችግሮች ለረዥም ጊዚያት ሳያድሱ የቆዩን ሁሉ ያካተተ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

በዚህ ሶት ወር ጊዜ ውስጥ ከዚህ ቀደም እስርና ቅጣት የተጣለባቸው የውጭ ዜጎች መቀጮ ሳይከፍሉና እስር ቤት ሳይገቡ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ይረዳል መባሉ ተሰምቷል፡፡

በተለይም በሃጅ  እና በኡምራ፤ በጉብኝት የገቡ ህገ ወጥ ነዋሪዎች ወደ የትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት መሄድ ሳጠበቅባቸው በቀጥታ ወደሃገራቸው መመለስ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን በባህር ፤ በአየርና በየብስ ወደ ሀገራቸው መግባት እንደሚችሉ ተገልፆል፡፡

 ከዚህ በተጨማሪ በኮንትራት መጥተው ከአሰሪያቸው የጠፉ ፤ ጠፉ ተብሎ የተከሰሱ ”በላቅ “ የተደረገባቸውና በመሳሰሉት መኖሪያ ፈቃዳቸው የተበላሸባቸውን ዜጎች ወደ ሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እየቀረቡ ጉዳያቸውን በመከወን ያለ መቀጮ በቀጥታ ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ በምህረት አዋጁ  ላይ መካተቱ ተዘግቧል፡፡

በሃጅ ስነ ስርአት  ወቅት ፈቃድ ሳይኖራቸው ሀጅ በማድረጋቸው ህግን የተላለፉና የተያዙና አሻራ ያደረጉም በዚህ ምህረት አዋጅ ያለ ቅጣት ወደ ሀገር መሄድ እንደሚችሉ ከሳውዲ መንግስት የወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

ለሶስት ወራት የተሰጠው የምህረት ጊዜ ህጋዊ ያልሆኑ ዜጎች ወደሃገራቸው ያለቅጣት እንዲመለሱ ለማድረግ እንጂ የመኖሪያ ፈቃዳቸው የተበላሸባቸው ዜጎች እንዲያስተካክሉ የወጣ አዋጅ ባለመሆኑ በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዬጲያውያን በዚህ የምህረት አዋጅ በመጠቀም ያለቅጣት ወደሃገር በመግባት ዳግም ወደ ሳኡዲ አረቢያ በህጋዊ የስራ ቪዣ መመለስ የሚችሉበትን ሁኔታ ሊያመቻቹ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ተጨማሪ ምስል