በማዕከላዊ ለወራት ታስረው የነበሩት በወንድም አልአሙዲን ኩመል የክስ መዝገብ የተከሰሱት 6 ሙስሊሞች የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት ተዘዋወሩ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 8/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአዲስ አበባ በደህንነቶች አማካኝነት ከስድስት ወራት በፊት ከቤተል እና አካባቢዋ ታድነው ወደ ማዕከላዊ ተወስደው ከነበሩት 9 ሙስሊሞች መካከል ስድስቱ ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ቂሊንጦ መዘዋወራቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ የሙስሊሙን ትግል ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን ከ 6 ወራት በፊትም 9 ሙስሊሞች ከአዲስ አበባ ከተማ በደህንነቶች ታፍነው በማዕከላዊ ታስረው እንደነበር ተዘግቧል፡: ሚያዚያ 20/2008 ቀን ለእስር መዳረጋቸውን የገለፁ ሲሆን በለሊት ለምረመራ በሚል ከእንቅልፋቸው እየተቀሰቀሱ መርማሪዎች ሲያሰቃዩዋቸው እንደነበር ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤትም ከፍተኛ ስቃይ እና ድብደባ ሲካሄድባቸው እንደነበር የተዘገበ ሲሆን አብረው ከታሰሩት 9 ሙስሊሞች መካከል ሶስቱ የሚሆኑትን ያለምንም ምክንያት ድንገት ከእስር ቤቱ እንዲፈቱ እንዳደረጓቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ የተፈቱት ሶስት ሙስሊሞችም የክስ መዝገቡ ተጠሪ የሆነው ወንድም አልአሙዲን ኩመል፣አብዲ ሸናኔ እና መካ መሐመድ መሆና ቸው ይታወቃ፡፡ በማዕከላዊ በነበሩበት ቆይታ አስጨናቂ እና የስቃይ ጊዜ ማሳለፋቸውን በወቅቱ የገለፁ ሲሆን ቀሪዎቹ 6 ሙስሊም ወጣቶችም ጉዳያቸው አላለቀም በሚል እስካሁን ሳይፈቱ እንደቀሩ ይታወቃል፡፡ ሳይፈቱ የቀሩትን 6 ሙስሊሞች የሽብር ክስ በማቅረብ ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 3 /2009 ላይ እንዲዘዋወሩ መደረጋቸው የታወቀ ሲሆን እነዚህም 1. ወንድም ነጃ ታጁ፣ 2. አብዱልፈታህ ሁንዴ፣ 3. አብዱልሃኪም አለዊ፣ 4. ዘይዱ ሙጂብ፣' 5. አቡበከር ሱሩር እና 6. ፉዓድ መሐመድ መሆናቸውን የፍትህ ራዲየየ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ እነዚህ 6 ሙስሊሞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተዘዋወሩ ሲሆን ማንኛውም ሙስሊም ወደ ማረሚያ ቤቱ በመሄድ ሊዘይራቸው እንደሚችል ተገልፆል፡፡ ሙስሊሙን የማሰር እና የማንገላታት ተግባሩ አሁንም እንደቀጠለ ነው