በማሻ ማቅደላ የሚገኘው ታላቁን መስጂደል ረህማንን ለማቃጠል የተደረገው ሙከራ መክሸፉ ተገለፀ


ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር13/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎዞን በማሻ መቅደላ የሚገኘውን ትልቁን መስጂደል ረህማንን ለማቃጠል የተደረገው ሙከራ መክሸፉን የአካባበው ሙስሊሞች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

ባሳለፍነው ጁምዓ  ከኢሻ ሰላት ቡኋላ ማንነተቸው ያልታወቁ ግለሰቦች መስጂዱን ለማቃጠል የሞከሩ ሲሆን በወቅቱ የመስጂዱ ጥበቃ የይድረሱልኝ ጥሪ በማሰማቱ የአካባቢው ማህበረሰብ በቦታው ደርሶ መስጂዱን ከቃጠሎ ማትረፍ መቻላቸው ተዘግቧል፡፡

በመቅደላ ወረዳ በአቶ ካሳ ፈቀደ እና በአቶ አለሙ አማካኝነት ከዚህ  ቀደም በወረዳው የሚገኙ  ቤተክርስቲያኖች  እንዲቃጠሉ ተደርገው በመቅደላ ወረዳ እጅግ በርካታ ሙስሊሞች ለግፍ እስራት እና ስቃይ መዳረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

በወረዳው ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን ለማጋጨት በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ሲሆን ቤተ እምነቶችን በማቃጠል የሁለቱን እምነት ተከታዬች ለማጋጨት እየተሞከረ መሆኑ ተገልፆል፡፡

በመስጂደል ረህማን የተደረገው የማቃጠል ሙከራ በተመሳሳይ በወረዳው በሚገኘው የደፈርጌ ቤተክርስቲያንንም   ለማቃጠል ተሞክሮ የቤተክርስቲያኑ የጥበቃ ሰራተኞች ሊያከሽፉት መቻላቸው ይታወቃል፡፡

በመቅደላ ወረዳ የመንግስት ካድሬዎች ባቃጠሉት ቤተክርስቲያን እስካሁን በርካታ ሙስሊሞች በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን  የአካባቢው ማህበረሰብ እውነታውን በመረዳቱ በሰላም ተከባብሮ እየኖረ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡

የዚህ መሰሉ ግጭት የመቀስቀስ ሂደቱ ወደ ጎጃምም እየተዛመተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የመንግስት ካድሬዎች ህዝቡ እርስ በእስር እንዳይተማመን ለማድረግ  ቤተ እምነቶችን በማቃጠል  ግጭት ለመቀስቀስ እየሞከሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

የዚህ መሰሉ ሴራ በተደጋጋሚ የተለያዩ ቦታዎች ሲፈጸም የቆየ በመሆኑ ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ የመንግስት ካድሬዎችን ሴራ በመረዳት የእምነት ቦታውን እና ጎረቤቱን ለቅቶ በመጠበቅ የጋራ ጠላት የሆነውን ሃይል ለመከላከል መጣር እንዳለባቸው ጥሪ መቅረቡ ተዘግቧል፡፡

በተያያዘ ዜናም በመቅደላ ወረዳ  ለተወሰነ አመት በፖሊስ  ኢኒስፔክተርነት ሲመራና የወረዳውን ማህበረሰብ  በክፍተኛ  ሁኔታ ለስቃይ ሲዳርግ የቆየው  ኢኒስፔክተር አንተነህ  ወደ አርጎባ  ተዘዋውሮ ቢሄድም በአርጎባ በነበረበት ወቅት ጁምዓ ምሽት በመሳሪ ተመቶ መገደሉ ተሰምቷል፡፡