በማረሚያ ቤት እሮብ እና ጁምዓ ቤተሰብ ጥየቃ እና ስንቅ ማቀበል የሚከለክለው መመሪያ ተግባራዊ መሆኑ ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 8/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ስር የሚገኙት ማረሚያ ቤቶች በሳምንቱ ቀናት ውስጥ እሮብ እና አርብ እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳገናኙ ለማድረግ የወጣው መመሪያ ተግባራዊ መደረግ መጀመሪን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አዲስ ባወጣው መመሪያ መሰረት እሮብ እና ጁምዓ የታሳሪ ቤተሰቦች እስረኞችን መጠየቅ የማይችሉ ሲሆን ከዚየራ ክልከላው በተጨማሪ በሁለቱ ቀናት ስንቅም ማቀበል እንደማይችሉ በመመሪያው መደንገጉ ተገልፆል፡፡
የክርስትና እምነት ተከታዬች ፆም መጠናቀቁን ተከትሎ ህገ ደንቡ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን መጪው የረመዳን ወር እየተቃረበ በመጣበት ወቅት የዚህን መሰሉን መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ሙስሊም እስረኞችን ለመጉዳት ታስቦ መሆኑ ተገልፆል፡፡
ቤተሰብ ጥየቃ እና ስንቅ ማቀበል የተከለከለው እሮብ እና ጁምዓ ቀን ሲሆን በሙስሊሞች የሳምንታዊ ኢድ በሆነበት የጁምዓ ቀን የቤተሰብ ዚያራ እና ስንቅ ማስገባት መከልከሉ መመሪያው በሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ አመላካች መሆኑ ታውቋል፡፡
እሮብ እና አርብ የክርስትና እምነት ተከታዬች የፆም ቀናቶች ሲሆኑ በተቃራኒው ጁምዓ ግን በሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ቀን ቢሆንም በዚሁ ቀን ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ እና ስንቅ እንዳይቀበሉ መደረጉ ሙስሊሙን በእምነቱ ለመጨቆን የተደረገ ለመሆኑ አጠያያቂ አለመሆኑ ተገልፆል፡፡
በህገ መንግስቱ መሰረት እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው፣ከህግ አማካሪዎቻቸው እና በሃይማኖት አባታቸው ጋር የመገናኘት መብት እንዳላቸው የተደነገገ ቢሆንም የማረሚያ ቤቶችአስተዳደር ግን ከህግ በላይ በመሆን በፈለገው ቀን የቤተሰብ ጥየቃን የመከልከል፣የፈለገውን ታሳሪ ሙሉ መብቱን የመግፈፍ ፣የፈለገውን ተግባር በእስረኞቹ ላይ የመፈፀሙን ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል፡፡
ይህ መመሪያ ይተገበራል ተብሎ ከተነገረ የቆየ ቢሆንም የክርስትና እምነት ተከታዬች ፆማቸውን እስኪያጠናቅቁ ተጠብቆ ተግባራዊ መደረጉ እና መጪውን የረመዳን ወር ለሙስሊሞች ታሳቢ ሳይደረግ መመሪያው ተግባራዊ መደረጉ ሙስሊም እስረኞችን መብት እንደሌላቸው እና አድሏዊ አሰራር መኖሩን በግልፅ ያመላከተ መሆኑ ተገልፆል፡፡
በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ከቤተሰብ የሚመጡ ስንቆችን ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥ እንዲሁም እንዲሞቅላቸውም ማድረግ የሚቻል የነበረ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ ይህን እስረኞች ሲደረግላቸው የነበረ ትብብርም እንዲቆም በማድረግ ከቤተሰብ የሚገባላቸው ምግብ አቆይተው እንዳይመገቡት እና እንዲበላሽ እያደረገባቸው መሆኑ ተገልፆል፡፡
ለሁለት ቀናቶች ከቤተሰብ ስንቅ መቀበል በተከለከለበት በዚህ ወቅት የእስረኛ ቤተሰቦች ቀደም ብለው ለሁለት ቀን የሚሆን ስንቅም ማስገባት እንዳይችሉ ማረሚያ ቤቱ በማቀዝቀዣ ውስጥ እንዲቀመጥላቸው እና አሙቀውም እንዲመገቡ የሚያስችላቸውን አሰራር እንዲቆም በማስደረጉ ትልቅ እንቅፋት እንደፈጠረባቸው የታሳሪ ቤተሰቦች ገልፀዋል፡፡
ይህን ከፍተኛ በደል እና ጭቆና ሁሉም ሊያወግዘው እንደሚገባ እና የሚመለከተው አካል ይህን ግልፅ የመብት ጥሰት እንዲያቆም ሁሉም የእስረኞችን ቁስል ተሰምቶት ድምፃቸውን ሊያሰማላቸው እንደሚገባ ጥሪ መቅረቡ ተዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል