በመካ ካዕባ አጠገብ እራሱን ለማቃጠል የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 30/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በሳኡዲ አረቢያ በተቀደሰችው በመካ ከተማ ኡምራ በማድረግ ላይ የነበረ ግለሰብ ካዕባ አጠገብ በመሆን እራሱን ለማቃጠል ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
ግለሰቡ የሳኡዲ ዜጋ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ካዕባ አጠገብ በመሆን እራሱን በቤንዚን አርከፍክፎ ለማቃጠል ያደረገው ሙከራ በሙስሊሙ እና በፖሊሶች ትብብር መክሸፉ ተዘግቧል፡፤
ግለሰቡ ይህን ተግባር የፈፀመው ካዕባ አጠገብ በመሆኑ ካዕባን ለማቃጠል ሙከራ እያደረገ እንደሆነ በማሰብ ጠዋፍ እያደረጉ የነበሩ ሙስሊሞች ተግባሩን በሃይል እንዳስቆሙት ታውቋል፡፤
ግለሰቡ ይህን ተግባር ለመፈፀም የተነሳሳው ወላጅ አባቱ ባለሃብት እና በርካታ ንብረቶች የነበሩት ሰው ሲሆን ወላጅ አባቱ ሲሞት የወላጅ አባቱ ወንድም ልጆቹን በተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም ሙሉ ለሙሉ ያባታቸው ንብረት በመንጠቁ ለተለያዩ አካላቶች አቤቱታውን ቢያቀርብም ሰሚ ባማጣቱ ትኩረት ለመሳብ ብሎ የፈፀመው መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ግለሰቡ ፍትህ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሊሳካለት ባለመቻሉ ካዕባ አጠገብ እራሱን በማቃጠል ትኩረት ለመሳብ እና ብሶቱን ለመግለፅ መሞከሩ ተሰምቷል፡፤
በወቅቱ በቦታው ላይ የነበሩ ጠዋፍ በማድረግ ላይ የነበሩ ሙስሊሞች በግለሰቡ ተግባር እጅግ የተበሳጩ ሲሆን በኢስላም ትልቅ ቦታ በሚሰጠው ቦታ ላይ የዚህ መሰሉን ተግባር መፈፀሙ ቁጣን ቀስቅሶበታል፡፡
የካዕባ ጠባቂ ፖሊሶች ግለሰቡን ከተግባሩ በማስቆም እያዳፉ የወሰዱት ሲሆን በቦታው በነበሩ ምዕመናን ዘንድ የመዲና መስጂድን በቦንብ ለማፈንዳት እንደተሞከረው ሁሉ ካዕባንም በእሳት ለማቃጠል ሙከራ እንደተደረገ በማሰብ ድርጉቱን በመቃወም ቁጣቸውን ሲገልፁ እንደነበር ተገልፆል፡፡
በመስጂደል ሃረም በካዕባ አጠገብ የተፈፀመው ተግባር ሌላ ተልዕኮ ይኑረው አልያ በብስጭት ትኩረት ለመሳብ ተብሎ የተደረገ ስለመሆኑ በሳኡዲ መንግሰት በኩል ተጣርቶ እስካሁን የተገለፀ ነገር አለመኖሩ ተዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል