ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ
የፌደራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት 7 ሙስሊም ወንድሞች ላይ ከ 4አመት እስከ 4 አመት ከ 5 ወር የሚደርስ እስራት ቅጣት በየነባቸው
ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 15/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በጃፈር መሐመድ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው በነበሩት 7 ሙስሊሞች ላይ የእስራት ቅጣት መበየኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
ሰባቱ ሙስሊሞች ከጅማ ከተማ ከ 3አመታት በፊት ለእስር የተዳረጉ ሲሆን በሶማልያ ከሚገኘው አልሸባብ ጋር ግንኙት ነበራቸው በሚል በሽብር መከሰሳቸው ታውቋል፡፡
ሰባቱ ተከሳሾች
1. ጃፈር መሐመድ፣
2. መሐመድኑር፣
3. ሃጂ መሐመድ ታሚ፣
4. ሙህዲን ጀማል፣
5. አህመድ አባቢያ ፣
6. አንዋር ትዳኔ እና
7. ሼኽጀማል አባ ጫቦ መሆናቸው ታውቋል፡
በኢትዬጲያ ውስጥ የጀሃድ ጦርነት ለማወጅ እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመሄድ ስልጠና ወስደዋል ሲል አቃቤ ህጉ የከሰሳቸው ሲሆን ከጅማ ከተማ ወደ ሶማልያ በመጓዝ ከአልሸባብ ጋር በመቀላቀል ስልጠና ሊወስዱ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲል አቃቤ ህጉ ክሱን አቅርቧል፡፡
ከ 3 አመታት በላይ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በ1ኛ፣በ4ኛ.በ5ኛ እናበ6ኛ ተከሳሾች ላይ 4አመት ከ 5 ወራት እስራት ቅጣት የበየነ ሲሆን በተቀሩት ሶስት ተከሳሾች ላይ ደግሞ የ4አመት ፅኑ እስራት እንደተበየነባቸው ተዘግቧል፡፡
መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብን በማሰር የግፍ ብይኑን ማስተላለፉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
ሃስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል

ተጨማሪ ምስል