ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ
በሳኡዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ያለቀረጥ ያፈሩትን ንብረት ወደ ሃገር ይዘው መመለስ እንዲችሉ የኢትዬጲያ መንግስት ፈቃድ መስጠቱ ተዘገበ
ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 9/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በሳኡዲ አረቢያ በተለያዩ መንገዶች ወደ ሃገሪቷ የገቡ እና የመኖሪያ ፈቃዳቸው በተለያዩ ምክንያቶች የተበላሹባቸው የውጪ ሃገር ዜጎች ቅጣት ሳይጣልባቸው በሰላም ወደሃገራቸው እንዲመለሱ የ 3 ወር የምህረት ጊዜ መሰጠቱን ተከትሎ ለረጅም ጊዜ ያፈሩትን ንብረት ወደሃገር ይዘው ለመግባት ከፍተኛ ቀረጥ የሚከፈልበት በመሆኑ ባዶ እጃቸውን ለመመለስ በመገደዳቸው መንግስት በነፃ ወደሃገር ንብረታቸውን ይዘው እንዲገቡ ፍቃድ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ዜጎች ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታቃል፡፡
በዛሬው እለት የኢትዬጲያ የጅዳ ቆንስል በፌስቡክ ገፁ ባሰራጨው መረጃ መሰረት የህብረተሰቡን ጥያቄ በመቀበል መንግስት ዜጎች ወደሃገራቸው ሲመለሱ ያለቀረጥ ያፈሩትን ንብረት ይዘው እንዲመለሱ መፍቀዱን ይፋ አድርጓል፡፡
የተለያዩ መገልገያዎችን እና የኤልክትሮኒክስ ምርቶችን ወደ ሃገራቸው ይዘው እንዲገቡ የተፈቀደ ሲሆን ያለቀረጥ ይዞ መግባት የሚቻሉትን የዕቃ እና መጠኑን ቆንስላው ይፋ ማድረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
ከነዚህ ከተፈቀዱ ቁሳቁሶች መካከል የጋዝ ምድጃ፣የፍራፍሬ መፍጫ፣የጋዝ ሲሊንደር፣ካሜራ፣ቪዲዬ ካሜራ፣ ላፕቶፕ፣ማጠቢያ ማሽን፣ቴሌቭዢን፣የፀጉር ካስክ፣ ፍርጅ፣ ሳተላይት ዲሽ ከነሬሲቨሩ፣ እና ሌሎችም ያለቀረጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ታውቋል፡፡
የወጥ ቤት ዕቃዎች፣ ካሜራዎች እና የኤሌክትሮኒስክስ ምርቶች ወደሃገር ያለቀረጥ ማስገባት የተፈቀደ ሲሆን ከሁሉም አይነት ንብረቶች ብዛት አንድ ብቻ መፈቀዱ ተገልፆል፡፡
ከአንድ በላይ ተመሳሳይ እቃ ያላቸው ዜጎች ወደሃገራቸው ንብረታቸውን ይዘው ለመሄድ ቀረጡን መክፈል እንደሚኖርባቸው አልያ ደግሞ ተቀናሽ ቀረጥ ስለመደረጉ የተገለፀ ነገረ አለመኖሩ የታወቀ ሲሆን ወደ ሃገር የሚመለሱ ዜጎች ለጊዜው ካላቸው የንብረት አይነት አንድ ብቻ ወደሃገራች ያለቀረጥ ይዘው መግባት እንዲችሉ መፈቀዱ ታውቋል፡፡
የብዙ ስደተኞች ጥያቄ የነበረው ያፈራነውን ንብረት እንዴት ጥለን ወደሃገር እንመለስ የሚል ሲሆን በተደጋጋሚ ከህብረተሰቡ የቀረበውን ስሞታ እና እሮሮ ምላሽ አግኝቶ ካፈሩት የተለያዩ ንብረቶች ላይ አንድ ፍሬ ብቻ በነፃ ወደ ሃገር እንዲያስገቡ መፈቀዱ ተዘግቧል፡፡
ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ወደሃገር እንዲመለሱ በተደረገው ቅስቀሳ 200 የሚጠጉ ኢትዬጲያውያን ብቻ መመለሳቸው የታወቀ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አብዛኛው ኢትዬጲያዊ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው በሳኡዲ አረቢያ ለመቆየት የወሰነ እንደሚመለስ እስካሁን ያለው እንቅስቃሴ አመላክቷል፡፡
ምናልባት ያለቀረጥ ወደሃገር ንብረታቸውን ይዘው እንዲገቡ መፈቀዱ ወደ ሃገር የሚመለሱትን ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎችን ቁጥር ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል ተዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል