ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ  

በዲላ ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች 4 መስጂዶች መቃጠላቸው ተዘገበ

ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 28/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በደቡብ ክልል በጌድኦ ዞን በዲላ ከተማ እና አጎራባች ከተሞች የሚገኙ 4 መስጂዶች በእሳት መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

መስጂዶቹ የተቃጠሉት በጌድኦ ብሄረሰብ በሆኑ የፕሮቴስታንት እምንት ተከታዬች ሲሆን በዞኑ የሚገኙ የጉራጌ፣የስልጤ እና  የአማራ ተወላጆች ንብረት  በእሳት መውደሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ 

የዚህ መሰሉ አሳዛኝ ድርጊት በይርጋጨፌ፣በዲላ፣ በወናጎ፣ በጨለለቅቱ/ኮቸሬ/ እና በሌሎችም በጌድኦ ዞን ስር በሚገኙ ከተሞች እየተፈመ መሆኑ የታወቀ ሲሆን የንግድ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች በእሳት እንዲወድሙ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

የጌድኦ ዞን በብዛት የፕሮቴስታንት እምነነት ተከታዬች ሲሆኑ የሌላ ብሄር ተወላጆችን ንብረት ከማውደም አልፎ የእምነት ተቋማትን ወደማውደም መሸጋገራቸው ተዘግቧል፡፡

በዲላ ከተማ 2 መስጂዶች መቃጠላቸው የተዘገበ ሲሆን በዲላ ዙሪያ በሚገኘው በቱምቲቻ ወረዳ አንድ መስጂድ እንዲሁም ከዲላ 15 ኪሎትር ርቀት ላይ በምትገኘው በዎናጎ ከተማም አንድ መስጂድ በጌዶኦ  ፕሮቴስታንቶች መቃጠሉ ን የአካባው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ 

በኮፌ የጋሞ መስጂድ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ የዋናው ካምፓስ መስጂድ በእሳት መቃጠሉ የተዘገበ ሲሆን   በወረዳው ብቸኛ የነበረው በቱምቲቻ ቀበሌ የሚገኘው  መስጂድም መቃጠሉ ተዘግቧል፡፡ 

የዚህ መሰሉ ዘርን  እና ሃይማኖትን ለይቶ የማጥቃት አፀያፊ  ተግባር ከ 9 አመት በፊት በዚሁ በጌድኦ ዞን ተፈፅሞ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ይህ ተግባር እንደ አዲስ በአሁኑ ወቅት በስፋት በዞኑ እየተፈፀመ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

በጌድኦ ዞን የጌድኦ ብሔረሰብ  ውስጥ ወደ 8000ሺህ የሚጠጉ ሙስሊሞች ቢኖሩም አብዛኛው ማህበረሰብ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች ሲሆኑ እምነትን እና ዘርን መሰረት በማድረግ ጥቃት እያደረሱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በዞኑ ይህ ሁሉ እልቂት እና ውድመት እየተፈፀመም የመንግስት ሃይሎች እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ለማስቆም ጥረት አለማድረጋቸው ድርጊቱ ከመንግስት በኩል የተቀነባበረ ለመሆኑ አመላካች ነው የተባለ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ያነሰውን ህዝብ በጥይት እየፈጁ ባለቤት በዚህ ወቅት እምነት እና ዘርን መሰረት በማድረግ በጌድዖ ዞን እየተፈፀመ የሚገኘውን ጅምላ ጭፍጨፋ  እና ጥቃት ለማስቆም አለመቻላቸው አሳዛኝ መሆኑ ተገልፆል፡፡ 

መንግስት ብሄርን ከብሄር፣ሃይማኖትን ከሃይማኖት  በማጋጨት ፖለቲካዊ ትርፍ ለማካበት በርካታ ጊዜ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አሁንም በደቡብ ክልል ተመሳሳይ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑ ታውቋል፡፡

ሃስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል