ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ

በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል  የተከሰሱት የደሴ ወጣቶች በሁሉም ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈባቸው

ፍትህ ራዲዬ/ታህሳስ 27/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በደሴ ከተማ ከ 3 አመት በፊት በመንግስት ደህንነቶች አቀናባሪነት የተገደሉትን ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል ሰበብ እና በሽብር ተግባ ላይ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከደሴ ከተማ ለእስር የተዳረጉት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ የሚገኙት  13 ወጣት ሙስሊሞች  በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት በዛሬው እለት ታህሳስ 27  የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው   እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

አቃቤ ህጉ ያቀረበባቸውን ሃሰተኛ ክስ ለመከላከል የሚያስችላቸውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ችሎትም ተከሳሾች ያቀረቡትን መከላከያ በመመርመር የመጨረሻ ብይን ለመስጠት የተሰጠ ቀነ ቀጠሮ ነበር፡፡

አቃቤ ህጉ በፀረ ሽብር አዋጅ 652/2001 አንቀጵ 6/1 እንዲሁም 6/7 በመወንጀል የተወሰኑትን ወጣቶች ሼህ ኑር ይማምን ገድላቹሃል፣ኢስላማዊ መንግስት ልትመሰርቱ ነበር እና በደሴ ከተማ ሲካሄዱ የነበሩ የሰደቃ እና አንድነት መድረኮች ላይ ተሳትፋቹሃል በማለት በሃሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወቃል፡፡

ፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ በመመርመር  የቀረበባቸውን  በፀረ ሽብር አዋጅ 652/2001 አንቀጵ 3 እና 1 እንዲሁም አንቀጵ 6 እና 7 በመተላለፍ የሚለውን ክስ  በመመርመር በሁሉም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በዛሬው ችሎት ማስተላለፉን የፍትህ ራዲየየ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ከመዝገቡ ተከሳሽ ከሆኑት መካከል በአምስቱ ላይ ቀርቦባቸው የነበረውም የሽብር ክስ ዝቅ በማድረግ በሌላ አነስተኛ አንቀፅ ጥፈተኛ በሚል ብይን ያስተላለፈባቸው ሲሆን እነሱም  አብዱራህማን እሸቱ ፣  ኢብራሒም ሙሔ ፣ እስማኤል ሀሰን .አብዱ ሀሰን፣ እና አህመድ ጀማል ሰይድ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በፀረ ሽብር ህጉ  ከፍተኛ የእስር ቅጣት በሚያስበይነው በአንቀፅ  4  አራት የሚሆኑት ወንድሞቻችን ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን እነሱም በሼህ ኑሩ ግድያ በቀጥታ ተሳታፊ ሆነዋል በሚል መሆኑ ተዘግቧል።እነዚህ አራት ሙስሊም ወንድሞቻችን በቅርቡ የቂሊንጦ ማ/ቤትን አቃጥለሃል በሚል ተጨማሪ የሽብር ክስ የተመሰረተበትን ወንድም ኡመር ሁሴንን ጨምሮ አንዋር ኡመር፣ ሷሊህ መሀመድ እና ይመር ሁሴን እንደሚገኙበት ተዘግቧ፡፡

በተቀሩት አራት ተከሳሾች ላይ ማለትም የመዝገቡ ተጠሪ አህመድ ኢድሪስ ፣ አደም አራጋው ፣ ከማል ሁሴን  እና ሙሀመድ ዩሱፍ  በፀረ ሽብር ህጉ በአንቀፅ 7/1 እና በአንቀጵ 5 ጥፋተኛ መባላቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ለ3 አመታት በቀነ ቀጠሮ ሲንጓተት የነበረው የፍርድ ቤት ሂደት በዛሬው እለት በሁሉም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ብይን በማስተላለፍ ውጤቱ የታወቀ ሲሆን ተከሳሾች እና አቃቤ ህጉ የቅጣት ማቅለኛ እና ማክበጃቸውን ለፍርድ ቤቱ እንዲያስገቡ  ትዕዛዝ በማዘዝ በጥር 9 የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔውን ለማስተላለፍ ቀነ ቀጠሮ መስጠቱ ተዘግቧል፡፡

በችሎቱ ተከሰሽ ኡመር ሁሴን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እየደረሰበት ያለውን  ግፍ እና መከራ አቤቱታውን ለችሎቱ ያቀረበ ከቤተሰቡ ጋር በችሎቱ እንዲገናኝ ትዕዛዝ ቢተላለፍም የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበር ከቤተሰቡ ጋር ሳያገናኙነት መቅረታቸው ተገልፆል፡፡

የደሴ ወጣቶች ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ህዝበ ሙስሊሙም  እንደተለመደው በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በመገኘት  አጋርነቱን ያሳየ ሲሆን በችሎቱም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም መገኘቱ ተዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል