በሜክሲኮ ተውፊቅ (ጀርመን) መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ መፈክሮች የተጻፉባቸው ወረቀቶች በማውለብለብ ድምፅ አልባ ተቃውሞ ተካሄደ!
አርብ መጋቢት 16/2008

ሙስሊሙ ህብረተሰብ መንግስት የጫነበትን ብሄራዊ ጭቆናን በመቃወም ዛሬም ሜክሲኮ አደባባይ አቅራኒያ በሚገኘው ተውፊቅ (ጀርመን) መስጂድ ከጁሙዓ ሰላት በኋላ ድምፅ አልባ ተቃውሞ አካሄደ!

በዚሁ ከጁሙዓ ሰላት በኋላ በተካሄደው ተቃውሞ የተለያዩ መፈክሮች የተጻፉባቸው ወረቀቶች የተውለበለቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ‹‹የነቃ ህዝብን ያሸነፈ አፈና የለም!››፣ ‹‹ሰላማዊ ያደረገን የአሚሮቻችን ቃል እንጂ የአምባገነን ጡጫ አይደለም!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!!!››፣ ‹‹ሰላም ከነሳችሁን ተመሳሳይ ኑሮ እንድንኖር ታስገድዱናላችሁ!!››፣ ‹‹ፍትህን ቀበሯት!!!››፣ ‹‹ትግላችን ይቀጥላል!!››፣ ‹‹እምነታችንን አናስንቅም!!›› እና ‹‹ድምፃችን ይሰማል!!›› የሚሉት ጎልተው የወጡ መሆናቸው ታውቋል።

እኒህ እና ሰሞኑን ሲካሄዱ የቆዩ ሰላማዊ ተቃውሞዎች በእርግጥም ብሄራዊ ጭቆናው ሳይቆም ሙስሊሙ ህብረተሰብ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል እንደማያቆም እና አራት ዓመታት የዘለቀው ሰላማዊ ትግልም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጫዎች ናቸው።

ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!

ምስል