በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ስቃይ ሲያስተናገዱ የነበሩት ሙስሊም እስረኞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዘዋወሩ

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር12/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳው እሳት ቃጠሎ ወደ ሸዋሮቢት ተዘዋውረው ከነበሩት እስረኞች መካከል ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ ሲያስተናግዱ የነበሩት ሙስሊም እስረኞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መመለሳቸውን የፍትህ ራዲዬ በልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ሙስሊም እስረኞቹ በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ውስጥ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን ያቃጠልነው እኛ ነን ብላችሁ እመኑ በሚል ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ሲፈፀምባቸው እንደነበር መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በአዲስ መልኩም ክስ ሊመሰርቱባቸው መዘጋጀታቸውን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ከሸዋሮቢት ወደ ቂሊንጦ ከተመለሱት መካከል

1 ኡስማን አብዶ

2 ሸህአብዲን ነስረዲን

3 ፍፁም ቸርነት

4 ኢብራሂም ካሚል

5 ከድር ታደለ

6 ኡመር ሁሴን

7 እስማኤል ሀሰን

8 ነዚፍ ተማም እንደሚገኙበት ታውቋል፡:

ከሸዋሮቢት ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ቢደረጉም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ከማዕከላዊ የመጡ መርማሪዎች ከፍተኛ ድብደባ በመፈጸም እና ፂማቸውን በመላጨት ሰብአዊ ክብራቸውን በጣሰ መልኩ ሲያሰቃዩዋቸው እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤቱን ያቃጠልነው እኛ ነን ብለው በግዳጅ እንዲናገሩ ሲደረጉ እንደነበር ይታወቃል፡፡

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በወቅቱ የተፈጠረውን ክስተት በግልፅ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ በማድረግ እና የተወሰነ ደቂቃ ብቻ እንዲገናኙ በማድረግ ጉዳዩን ለማፈን ጥረት ሲደረግ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን አሁንም ከሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት የተመለሱትን ሙስሊም እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ የተፈፀመባቸውን ነገር ይፋ እንዳይሆን እያከላከሉ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡

በተያያዘ ዜናም በእስር ላይ ሆኖ በጠና ታሞ የነበረው ጋዜጠና ዳርሰማ ሶሪ ህክምናውን ለከታተል በሚል ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዋወር ተደርጎ የነበረ ሲሆን ዳግም ወደነበረበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊመለስ መሆኑን ምንጮች ለፍትህ ራዲዬ ገልጸዋል፡፡

መንግስት እስረኞችን በአግባቡ የመያዝ ግዴታ ቢኖርበትም እስረኞች ባልሰሩት ወንጀል መከሰሳቸው ሳያንስ በድብደባ እና በስቃይ ሌላ ተጨማሪ ግፍ በእስረኞች ላይ እየፈፀመ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡