ታላቁ የደሴ አሊም አባባ ሼኽ አደም ወደ አኼራ ሄዱ

Posted on Mar 6, 2016

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

ፍትህ ራዲዬ/የካቲት 26/2008 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በደሴ ከተማ በአረብ ገንዳ መስጂድ ከ 40 አመት በላይ በኢማምነት እና ህዝበ ሙስሊሙን በቁርአን ተፍሲር እና በሌሎች ኢስላማዊ ትምህርቶችን በማስተማር የሚታወቁት ታላቁ አሊም ሼኽ አደም ሙሳ(አባባ አደም) ባደረባቸው ግመም በኢትዬ ጠቢብ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኼራ መሄዳቸው ታውቋል፡፡

በደሴ ከተማ ሙስሊሙም ሆነ የሌላ...

በቦረና ዞን የምትገኘው ያቤሎ ከተማ በግራፊቲ ጽሑፎች ተጥለቅልቃ አደረች!

Posted on Mar 4, 2016

ሰበር ዜና!!! ‹‹ለበደል እጅ አንሰጥም!›› የሚሉ ድምጾች ተጠናክረው ቀጥለዋል! አርብ የካቲት 25/2008

በቦረና ዞን በምትገኘው ያቤሎ ከተማ ሌሊቱን የግራፊቲ ፅሁፎች ተጽፈው አደሩ! የሕዝቡን ተቃውሞ የሚያሳዩ መፈክሮች እና ጽሁፎች ተበትነው እና በስልክ እንጨቶች ላይ ተለጥፈው ባደሩበት በዚሁ ተቃውሞ የከተማው ደህንነቶች የተደናገጡ ሲሆን መፈክሮቹን በመገንጠል እና በማጥፋት ላይ ተሰማርተው ያረፈዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከተጻፉት መፈክሮች...

ለደሴ ከተማ ሙስሊሞች ምስክር ለመሆን ወደ ቃሊቲ ማ/ቤት የመጡት...

Posted on Mar 4, 2016

ለደሴ ከተማ ሙስሊሞች ምስክር ለመሆን ወደ ቃሊቲ ማ/ቤት የመጡት በነኤልያስ የክስ መዝገብ የሚገኙት ሙስሊሞች ፂማቸውን እንዲላጩ ማ/ቤቱ ጫና ሲያደርግባቸው እንደነበር ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/የካቲት 25/2008 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በሃሰት የሽብር ወንጀል ተመስርቶባቸው የ 7 አመታት የግፍ እስራት የተበየነባቸው በኤልያስ ከድር መዝገብ የሚገኙት ሙስሊሞች በሼህ ኑሩ ግድያ በሃሰት ለተወነጀሉት የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች የመከላከያ ምስክር...

በአማን አሰፋ መዝገብ የጥፋተኝነት ብይን የተሰጠባቸው ሙስሊሞች ....

Posted on Mar 3, 2016

በአማን አሰፋ መዝገብ የጥፋተኝነት ብይን የተሰጠባቸው ሙስሊሞች የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔያቸውን ለመስማት ለየካቲት 30 ቀነ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ፍትህ ራዲዬ/የካቲት 24/2008 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በኢትዬጲያ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል በሚል በነ አማን አሰፋ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሙስሊሞች የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በ 24ቱ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ካስተላለፈ ቡሃላ በዛሬው ዕለት የመጨረሻ የቅጣት...

የብሄራዊው ጭቆና ዋነኛ መገለጫዎች ምን ምን ናቸው? (ባለቀጣይ ክፍል)

Posted on Feb 29, 2016

ተከታታይ ግንዛቤ ማስጨበጫ - ክፍል 3 ሰኞ የካቲት 21/2008

በተከታታይ ከሚወጣው የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሁፍ ክፍል አንድ እና ሁለትን ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ በክፍል አንድ የአህባሽ አመለካከት በመንግስት ሃይል መጫን ከብሄራዊ ጭቆናው መገለጫዎች አንዱ መሆኑን ያየን ሲሆን በክፍል ሁለት ደግሞ ከመደራጀት መብቶች እና መንግስት ከሚያደርገው የማጠልሸት ዘመቻ ጋር የተያያዙ 3 ነጥቦችን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡ ዛሬ ደግሞ በአላህ ፈቃድ አምስተኛውን የብሄራዊ...

በፍልውሃ (ተውፊቅ) መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ ተቃውሞ ተካሄደ!

Posted on Feb 26, 2016

ሰበር ዜና!!! መፈክሮች የተጻፉባቸው ባሉኖች ተውለብልበዋል! አርብ የካቲት 18/2008

በፍልውሃ (ተውፊቅ) መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ ተቃውሞ ተካሄደ!

ከጁሙዓ መልስ በተካሄደው በዚሁ ተቃውሞ መፈክሮች የተጻፉባቸውን ባሉኖች ተውለብልበው ወደሰማይ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡ በባሉኖች ላይ ከተጻፉት መፈክሮች መካከል ‹‹ብሄራዊ ጭቆናን እንታገላለን!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድራማው ይብቃ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› እና ‹‹ጭቆናው ይብቃ!››...

በአንዋር መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ ታላቅ የድምጽ ተቃውሞ ተካሄደ!

Posted on Feb 19, 2016

ሰበር ዜና!!! አርብ የካቲት 11/2008

ዛሬ የካቲት 11/2008 በአንዋር መስጂድ ከጁሙዓ መልስ የድምጽ ተቃውሞ ተካሄደ! ባለፈው ሳምንት ከተደረገው የጽሁፍ መፈክር የማሳየት ተቃውሞ በኋላ መንግስት ወደመስጊዱ የሚመጣውን ሰው በፍተሻ ሲያጉላላ የነበረ ቢሆንም የድምጽ መፈክሮች በድምቀት ተሰምተዋል!

ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ብሄራዊ ጭቆናው እስኪገታ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም በተደጋጋሚ ሲገልጽ የቆየ ሲሆን በዛሬው ተቃውሞውም ‹‹ብሄራዊ ጭቆናው...

txdvioawpf01
sfy39587stp17
sfy39587stp16