አህባሽ መራሹ መጅሊስ በፌደራል ፖሊስ እና በደህንነቶች በመታጀብ በሼህ ሆጀሌ መስጀድ አዲስ የጥበቃ ሰራተኛ በጉልበት ማስገባቱ እና የመስጂዱን በር ቁልፍም በጉልበት መቀየራቸው ታወቀ

Posted on Apr 11, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 2/2008 በህዝበ ሙስሊሙ መዋጮ የተገነባው ታላቁ የሼህ ሆጀሌ መስጂድ በግዳጅ ለአህባሽ መራሹ መጅሊስ መንግስ በፍርድ ቤቱ በኩል እንዲሰጥ ካደረገ ወዲህ መስጂዱን ሙሉ ለሙሉ ከሙስሊሙ በመንጠቅ የአህባሽ ማሰራጫ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተጠናከሮ መቀጠሉን ፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት አህባሾቹ ከፍተኛ ግብረሃይል በማሰባሰብ ወደ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ በመሄድ በጉልበት የመስጂዱን ቁልፍ በጉልበት መረከባቸው ተዘግቧል፡፡ የአህባሽ...

ህገ ወጡ የፌደራሉ መጅሊስ ለ3ቀናት የሚቆይ የአህባሽ ስልጠና በኡማ ሆቴል እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለፀ

Posted on Mar 30, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መጋቢት 202008 አህባሽ መራሹ የፌደራሉ መጅሊስ ከሁሉም ክልል የተውጣጡ የአህባሽ ኡለሞችን በመሰብሰብ አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ሽፋን ለ ሶስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በኡማ ሆቴል እየሰጠ እንደሚገኝ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ከመጋቢት 19-21-2008 በሚቆየው በዚህ ሃገር አቀፍ ስልጠና ላይ ከዚህ ቀደም የአህባሽ ስልጠና ሲሰጥ በስልጠናው መጀመሪያ ላይ ለሁሉም ሰልጣኞች የሚሰጠውን አክራሪነትና ፅንፈኝነት ከህገ መንግሥቱ...

ሕዝበ ሙስሊሙ ዛሬም ለፍትህ የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁን ቀጥሏል!

Posted on Mar 26, 2016

በሜክሲኮ ተውፊቅ (ጀርመን) መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ መፈክሮች የተጻፉባቸው ወረቀቶች በማውለብለብ ድምፅ አልባ ተቃውሞ ተካሄደ! አርብ መጋቢት 16/2008

ሙስሊሙ ህብረተሰብ መንግስት የጫነበትን ብሄራዊ ጭቆናን በመቃወም ዛሬም ሜክሲኮ አደባባይ አቅራኒያ በሚገኘው ተውፊቅ (ጀርመን) መስጂድ ከጁሙዓ ሰላት በኋላ ድምፅ አልባ ተቃውሞ አካሄደ!

በዚሁ ከጁሙዓ ሰላት በኋላ በተካሄደው ተቃውሞ የተለያዩ መፈክሮች የተጻፉባቸው ወረቀቶች የተውለበለቡ ሲሆን...

«ሦስቱ አፄዎችና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች» የተሰኘው የኡስታዝ አህመዲን ጀበል መጽሐፍ በደማቅ ሁኔታ በጅዳ ከተማ ተመረቀ

Posted on Mar 25, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መጋቢት 16/2008

በእስር ላይ በሚገኘው በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል እና በታሪክ ምሀሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተዘጋጀው ሶስቱ አፄዎች እና ኢትዬጲያን ሙስሊሞች (ትግልና መስዋትነት)የተሰኘው መፅሃፍ በሳኡዲ አረቢያ በጅዳ ከተማ ስ በደማቅ ሁኔታ ትላንት ሃሙስ ማርች 24 መመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

መፅሃፉ ለንባብ በቀረበ በአጭር ቀናቶች ውስጥ በሃገር ውስጥ የመጀመሪያው እትም...

በሳኡዲ አረቢያ በመካ ከተማ አሕባሽ መራሽ የሆነ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ለማቋቋም የኢሕአዴግ መንግስት እያደረገ ያለው ጥረት ህዝቡ እንዲያከሽፈው ጥሪ ቀረበ

Posted on Mar 18, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መጋቢት 9/2008

በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ኮሚኒቲዎችን በመሰነጣጠቅ አህባሾችን ሰርጎ በማስገባት የአህባሽ መራሽ ኮሚኒቲ በየከተማው ለማቋቋም የኢህአዴግ መንግስት ጥረት እያደረገ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በጅዳ ኮሚዩኒቲ ተጠቃሎ የሚገኘው የመካ ከተማን ኢትዮጵያዊ ለብቻው ኮሚዩኒቲ እንዲያቋቁም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በጅዳ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ዲፕሎማቶች የሚመራው ጥረት የመካን ህዝብ...

በታላቁ አንዋር እና ኑር መስጂዶች ዙሪያ ከፍተኛ ፍትሻ እና ውክቢያ በወታደሮች ሲፈጸም እንደነበር ተዘገበ

Posted on Mar 18, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መጋቢት 9/2008

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለተከታታይ ጁምአዎች ባደረጋቸው ድንገተኛ ተቃውሞዎች የተደናገጠው መንግስት በዛሬው ጁምአም ድንገተኛ ተቃውሞ እንዳያደርግ ለማሸማቀቅ በሚል በታላቁ ኑር መስጂድ እና በታላቁ አንዋር መስጂድ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ ሲያካሂድ እንደነበር ሪፖርተራቸው ከቦታቸው ዘግቧል፡፡

በዛሬው ዕለት በታላቁ ኑር መስጂድ እና በአንዋር መስጂድ ዙሪያ በከባዱ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአዲስ...

መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ የማህበራዊ ሚዲያዎችን መዝጋቱ ተገለጸ

Posted on Mar 18, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መጋቢት 9/2008 በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ መንግስት ማህበራዊ ሚዲያዎችን መዝጋቱን ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማዳከም እና የሙስሊሙን ትግል ለማዳከም በማሰብ መንግስት ህዝቡ መረጃዎችን ይለዋወጡበታል የሚላቸውን ማህበራዊ ሚዲያዎች በሻሸመኔ ከተማ መዝጋቱ ታውቋል፡፡ ህዝቡ በብዛት የሚጠቀምበት የነበረውን Whats Up አገልግሎት እንዲዘጋ መንግስት ያደረገ ሲሆን VIber፣IMO፣...
txdvioawpf01
sfy39587stp17
sfy39587stp16