በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ ኡለሞች እና ኡስታዞች በእስር እየተሰቃዩ መሆኑ ታወቀ

Posted on Oct 4, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 24/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በራያ አዘቦ ኡለሞች እና ኡስታዞች ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ለእስር ተዳርገው በስቃይ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

ኡለሞቹ እና ኡስታዞቹ በራያ አዘቦ ወረዳ ኩኩፍቶ በተባለ ቦታ የተያዙ ሲሆን ማይጨው በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ከታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች መካከል...

መንግሥት አሁንም በእብሪተኝነቱ ቀጥሏል!

Posted on Aug 4, 2016

እኛም እስከመጨረሻው በፅናት ከመታገል ውጭ ሌላ አቋራጭ መንገገድ የለንም! ሐሙስ ሐምሌ 28/2008

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መንግስት መራሹን ሃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት ስንታገል ይኸው ዓመታትን አሳልፈናል፡፡ በዚህ ወቅት ሁሉ መብታችንን በዘላቂነት ለማስከበር በጽናት የቆምን ሲሆን በሂደትም ዘርፈ ብዙ ልምድን፣ ጠንካራ የእምነት ትስስርን እና መደጋገፍን መሠረት ያደረገ ወንድማማችነት መመስረት ችለናል። በዚህም እኛን ለመከፋፈል የተደረጉ የመንግስትን በርካታ...

የቂሊንጦ ማ/ቤት አዲሱን የታሳሪዎች ቱታ የዞን 2 ታሳሪዎች እንዲለብሱት አደረገ

Posted on Aug 4, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሃምሌ 28/2008

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በቅርቡ በማረሚያ ቤቱ ታስረው ለሚገኙ እስረኞች አዲስ የእስረኞች ቱታ እያዘጋጀ መሆኑን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች ታስረው ለሚገኙት እሰረኞች አዲሱ ቱታ እንደተሰጣቸው የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታሰረው ከሚገኙ እስረኞች መካከል በዞን ሁለት የሚገኙት እስረኞች አዲሱን ቱታ በዛሬው እለት እንዲለብሱት የተደረገ...

ፍትህ በኢትዮጵያ የተቀበረባት፣ ለፍትህ ፈላጊው ሙስሊም የትግል ጽናት ግድ የሆነባት ቀን!

Posted on Aug 3, 2016

ሐምሌ 27 ረቡእ ሐምሌ 27/2008

በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የትግል ሂደት ውስጥ ወርሃ ሐምሌ ልዩ ቦታን ይዞ የሚገኝ ወር ነው። የአገሪቱን ህጎች ጠብቆ እና አስጠብቆ ሰላማዊ በሆነ ልዩ ስርዓት ፍትህን ለማግኘት ድፍጹን ከፍ በማድረግ ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የሚል ጥሪ ባደረገ ህዝብ ላይ የጥቁር ሽብር የታወጀበት እና የተፈጸመበት ወር ብቻ ሳይሆን ይህን የፍትህ ፈላጊነት መርሁን ሳይለቅ ጥያቄዎቹ እስከሚመለሱበት ቀን ድረስ ትግሉን እንደሚቀጥል ቃል...

በወራቤ ከተማ የሚገኘውን የአቡበከር ሲዲቅ ኢስላማዊ ኮንፕሌክስ ለመታደግ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በሪያድ ከተማ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ

Posted on Aug 3, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሃምሌ 27/2008

በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ በ ሃጂ አብዱልሃዲ ኣማካኝነት 1996 የተገነባው የመጀመሪያው ኢስላማዊ ተቋም አቅሙን በማሳደግ ከፍተኛ ስራዎችን ለመስራት ላቀደው እቅድ ማሳኪያ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ሃሙስ በሪያድ ከተማ ማዘጋጀቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የአቡበከር ሲዲቅ ኢስላማዊ ተቋም ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ተማሪዎችን ተቀብሎ በተለያዩ...

በአማሪካ የ ነጃሺ ሳንድያጎ ጀመአዎች በእስር ላይ ለሚገኙት ኮሚቴዎቻችን የምስክር ወረቀት ሽልማት አበረከቱ

Posted on Jul 22, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሃምሌ 12/2008

በአሜሪካ በሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ የሚገኘው ነጃሺ ጀምዓ የኢ አል ፊጥር በዓልን በማስመልከት ባሳለፍነው እሁድ ጁላይ 17 ልዩ ፕሮግራም ማዘጋጀቱ የታወቀ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይም ለኮሚቴዎቻችን የክብር የምስክር ወረቀት ከጀምዓው እንደተበረከተላቸው የጀምዓው አሚር ለፍትህ ራዲዬ ገልፆል፡፡

ዝግጅቱ የኢድ አል ፊጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ በጋራ በደስታ በዓሉን ለማክበር የተዘጋጀ ሲሆን የተለያዩ...

በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱት 20 ሙስሊሞች ለብይን ለጥቅምት 9 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Jul 22, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሃምሌ 15/2008

በደህንነቶች ከያሉበት ታፍነው ለእስር የተዳረጉት በከድር መሐመድ የክስ መዝገብ የሚገኙት 20 የአዲስ አበባ እና የጅማ ከተማ ሙስሊሞች በዛሬው እለት ሐምሌ 15 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በጸረ ሽብር አዋጁ ክስ የቀረበባቸው እነዚህ ወጣት ሙስሊሞች አቃቤ ህጉ ላቀረበው ክስ የስረዱልኛል ያላቸውን 30 የሰው እና ተያያዝ ምስክሮች ለፍርድ...

txdvioawpf01
sfy39587stp17
sfy39587stp16