ከኮፈሌ ከተማ በሻሸመኔ ማረሚያ ቤት ሳይፈቱ በግፍ ታስረው የነበሩት አምስት ሙስሊሞች መፈታታቸው ተዘገበ

Posted on May 12, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 4/2008

በአሮሚያ ክልል በኮፈሌ ከተማ መንግስት በሙስሊሙ ላይ የወሰደውን ጅምላ ጭፍጨፋ ተከትሎ ለአመታት በእስር ሲሰቃዩ የነበሩት 5 ንፁሃን ሙስሊሞች በዛሬው ዕለት ከእስር መለቀቃችን የፍትህ ራዲዬ ባልደቦች ዘግበዋል፡፡

ከሁለት አመት በፊት በሃምሌ 27 መንግስት በከተማዋ ሙስሊሞች ላይ ጥይት በመተኮስ በርካቶችን መግደሉ እና ማቁሰሉ የሚታወስ ሲሆን የተፈጠረውን ረብሻ ተከትሎም በርካቶች ወደ እስር ቤት...

በሼህ ኑሩ ግድያ ለተወነጀሉት የደሴ ከተማ ሙስሊሞች ወንድም ኤልያስ ከድር እና ዩሱፍ መሐመድ የምስክር ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ ሰጡ

Posted on May 12, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 4/2008

ከደሴ ከተማ በሽብር ወንጀል ተከሰው የመከላከያ ምስክራቸውን ለፍርድ ቤቱ እያስደመጡ የሚገኙት 13ቱ ደሴ ከተማ ሙስሊሞች በዛሬው ዕለት ግንቦት 4 ሁለት ምስክሮቹን ለፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ማስደመጣቸውን ፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በትላንትናው ችሎት የዞን 9 ጦማሪ የሆነውን በፍቃዱ ዘሃይሉ ፍርድ ቤት በመቅረብ ለተከሳሽ እስማኤል ሃሰን የመከላከያ ምስክር በመሆን...

በሼህ ኑሩ ግድያ የተወነጀሉት የደሴ ከተማ ሙስሊሞች የዞን 9ጦማሪ የሆነውን በፍቃዱ ዘሃይሉን ጨምሮ ሁለት ምስክሮችን ለፍርድ ቤቱ አስደመጡ

Posted on May 11, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 3/2008

በደሴ ከተማ ከ 2 አመት በፊት በመንግስት ደህንነቶች አቀናባሪነት የተገደሉትን ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል ሰበብ ከደሴ ከተማ ለእስር የተዳረጉት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ የሚገኙት ሙስሊሞች 13 ወጣት ሙስሊሞች አቃቤ ህጉ ባቀረበባቸው የሽብር ክስ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ በወሰነባቸው መሰረት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ለፍርድ ቤቱ እያስደመጡ ሲሆን ቀሪ ምስክሮቻቸውን ለፍርድ ቤቱ ለማሰማት በዛሬው ዕለት እሮብ ግንቦት 3...

በአፋር ክልል የአሳይታው ቢላል መስጂድ ግንባታን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርርበ እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ

Posted on May 10, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት2/2008 በአፋር ከልል የአይሳኢታው ቢላል መሰጅድን ግንባታ እሰከ ነህሴ 30/2008 ድረሰ ለመጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተካሄደ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በታላቁ ሰሀባ በሃበሻዊው ቢላል ስም የተሰየም የረህ ባለ ፎቅ መስጂ ተገንብቶ ባጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጥ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ሙስሊሙ ማህረሰብም መስጂዱን ለማጠናቀቅ አቅሙ በፈቀሰደው መልኩ ድጋፍ እንዲያደግ አሰረ ኮሚቴዎቹ ጥሪ...

በአዳማ ከተማ ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

Posted on May 8, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 30/2008 በኢድ ሰላት በሚሰገድበት በአዳማው ኡመር መስጂድ ታላላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ዝግጅቱ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አስተበባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን ታላላቅ ዳዒያንም በእንግድነት ተጋብዘዋል፡፡

ዝግጅቱ በየአመቱ የሚካሄድ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይም ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ፣ ኡስታዝ መሀመድ ፈረጅ፣ኡስታዝ ሃይደል እና ሌሎችም ተካፍለዋል...

የሼኽ ሆጀሌ መስጂድ የቀድሞ ኮሚቴ የነበሩት ሼህ ዩሱፍ ሙዘሚልን ጨምሮ 6 ሙስሊሞች ከጁምዓ ሰላት በኋላ ትፈለጋላችሁ በሚል በፖሊስ መወሰዳቸው ተዘገበ

Posted on May 6, 2016

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 28/2008

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የሆኑት እና የሼህ ሆጀሌ መስጂድን ከ 20 አመት በላይ በአስተዳዳርነት የመሩት ሼህ ዩሱፍ ሙዘሚልን ጨምሮ 6 ሙስሊሞች ከጁምዓ ሰላት ቡሃላ በፖሊሶች ተፈለጋላችሁ በሚል ወደ ፖሊስ ጣብያ መወሰዳቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ህገ ወጡ አዲስአበባ መጅሊስ መስጂዱንበጉልበት ከተረከቡ ወዲህ መስጂዱንለማዳከም የተለያዩ...

በነብዩ ሲራጅ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች የአቃቤ ህጉ ምስክሮችን ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ለግንቦት 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Apr 28, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 20/2008

ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች ለእስር የተዳረጉት በነብዩ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ዛሬ ሚያዚያ 20 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በ ሚያዚያ 5 በነበራቸው ቀነ ቀጠሮ አቃቤ ህጉ ምስክሮቹን ሊያቀርብ ባለመቻሉ ለዛሬ ሚያዚያ 20ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

...

txdvioawpf01
sfy39587stp17
sfy39587stp16