በምዕራብ ሀረርጌ ሂርና ከተማ ሁዳ የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል 17 የቁርአን ሀፊዞችን አስመረቀ

Posted on May 22, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 13/2008

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሃረርጌ በሂርና ከተማ 17 የሚሆኑ የቁርአን ሃፊዞችን ሁዳ የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል ማስመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባክደረቦች ዘግበዋል፡፡

ከ 10ሺህ ህዝብ በላይ በተገኘበት በዚህ ልዩ የምረቃ ስነ ስአት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም የካፈሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል ተወዳጁ ኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ፣ ኡስታዝ ሃይደር ከድር ፣ ኡስታዝ ራያ አባሜጫ ፣ጋዜጠኛ ዩሱፍ ከድር እና...

ኢብኑ ከሲር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል 128 የቁርአን ሃፊዞቹን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ

Posted on May 22, 2016

አስደሳች ዜና ፍትህ ራዲዬ

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 13/2008

በአዲስ አበባ በጉልለሌ ክ/ከተማ በሼህ ሆጀሌ መስጂ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው የኢብኑ ከሲር ቁረአን ሂፍዝ ማዕከል ለ 2 አመት ሲያስተምራቸው የቆውን ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት እሁድ ግንቦት 14 በአምባሳደር ቲያትር አዳራሽ ማስመረን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኢብኑ ከሲር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል በዘንድሮ አመት ሲያስመርቅ ለ4 ኛ ጊዜ መሆኑ...

ኢብኑ ሰኪር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል የፊታችን እሁድ በአምባሳደር ቲያትር አዳራሽ ቁርአን ሃፊዞቹን እንደሚያስመርቅ አስታወቀ

Posted on May 20, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 12/2008 በአዲስ አበባ በጉልለሌ ክ/ከተማ በሼህ ሆጀሌ መስጂ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው የኢብኑ ከሲር ቁረአን ሂፍዝ ማዕከል ለ 2 አመት ሲያስተምራቸው የቆውን ተማሪዎቹን የፊታን እሁድ ግንቦት 14 ሊያስመርቅ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኢብኑ ከሲር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል በዘንድሮ አመት ሲያስመርቅ ለ4 ኛ ጊዜ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከል የማዕከሉ የመጀመሪያ ሴት ተመራቂዎች...

የትግላችን መሰረት ህዝባችን ነው እና ህዝባችንን ተደራሽ ለማድረግ የምናደገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

Posted on May 18, 2016

ረቡእ ግንቦት 10/2008

ትግል ክስተት ሳይሆን ሂደት ነው፡፡ ይህን ሂደት የሚፈጥሩትም ሆነ ከዳር የሚያደርሱት ደግሞ የትግሉ ባለቤት የሆኑት ህዝቦች ናቸው፡፡ እንደአገራችን ባሉ ዲሞክራሲ ባልዳበረባቸው አገራትና አሁን ባለው አለም አቀፍ ተለዋዋጭ ፓለቲካ የትግል ሂደት እንደ ሜዳ ለጥ ያለና የተደላደለ አይደለም፡፡ እንቅፋትና አሜኬላ የበዛበት፣ በዳገትና ቁልቁለት የተሞላ ነው፡፡ የትግሉ ባለቤቶች በእነዚህ የትግል ተፈጥሯዊ ሂደቶች ውስጥ ሲያልፉ...

በአንድ ብር አንድ ታሳሪ ወገንን እናስፈጥር በሚል መርህ በድር ኢትዬጲያ ታላቅ ዘመቻ መጀመሩን አስታወቀ

Posted on May 16, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 8/2008

መቀመጫውን ሰሜን አሜሪካ ያደረገው ከኢትዬጲያ ውጪ የሚገኙ ሙስሊም ኮሚኒቲዎችን አቅፎ የያዘው ግዙፉ የሙስሊም ኢትዬጲያውያን ድርጅት የሆነው በድር ኢትዬጲያ ከፊታችን እየመጣ የሚገኘውን የታላቁ የረመደን ወር በማስመልከት በሃገር ቤት በእስር ላይ የሚገኙ ሙስሊሞችን ወሩን ሙሉ ለማስፈጠር ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል፡

በድር ኢትዬጲያ በስሩ ባቀፍቸው እህት ኮሚኒቲዎች ጋር በመሆን...

ሶስቱ አፄዎች እና ኢትዬጲያን ሙስሊሞች (ትግልና መስዋትነት)የተሰኘው የኡስታዝ አህመዲን ጀበል መፅሃፍ በደማቅ ሁኔታ በግብፅ ካይሮ ተመረቀ

Posted on May 15, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 6/2008

በእስር ላይ በሚገኘው በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል እና በታሪክ ምሀሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተዘጋጀው ሶስቱ አፄዎች እና ኢትዬጲያን ሙስሊሞች (ትግልና መስዋትነት)የተሰኘው መፅሃፍ በግብፅ ካይሮ በትላንትነው ዕለት ጁምዓ ግንቦት 5 በደማቅ ሁኔታ መመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ከሃገር ማዶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሳኡዲ አረቢያ በሪያድ ከተማ የተመረቀ ሲሆን በቀጣይም...

የየቲሞች አባት ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ታወቀ

Posted on May 13, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 5/2008

በኡስታዝ አቡበከር አህመድ የክስ መዝገብ ተከሶ የ 7 አመት የግፍ እስራት የተበየነበት ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ከደህንቶች ተልዕኮ በተሰጠው ታሳሪ ግለሰብ በመቆፈሪያ አንገቱን ከተወጋ ቡሃላ በአንገቱ ላይ ከደረሰበት ጉዳት በአሁኑ ወቅት አገግሞ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በህግ ጥላ ስር ሆኖ የዚህ መሰሉ ጥቃት ስለደረሰበት...

txdvioawpf01
sfy39587stp17
sfy39587stp16